Get Mystery Box with random crypto!

[አሊጎሪ] # _ናታን_ኤርሚያስ ተረዱት : ያንን : ሰው ፣ . . መቆሚያ ለጠፋው መንገድ ለራ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

[አሊጎሪ]
# _ናታን_ኤርሚያስ

ተረዱት : ያንን : ሰው ፣
.
.
መቆሚያ ለጠፋው መንገድ ለራቀበት፣
ምስራቅ እየወጣ ምዕራብ ለጠፋበት፣
የብርሀኑን አስኳል ፅልመት ለወረረው፣
እልፍ ግዜ ወድቆ እጦት ላሳረረው ፣

["እህ" በሉት እስቲ
ተረዱት ያንን ሰው...
.
.
ምግባሩ ከሀሳቡ ጠቦ ያልገጠመ፣
እቺን አለም ሰምቶ ሳይዋኝ ለሰጠመ፣
እፈታለሁ ብሎ ላየው እንቆቅልሽ፣
አይኑ የታወረበት ሳይፈታው ለትንሽ፣
ዛሬም ድግግሞሽ በምኞት ተጋርዶ፣
እሚረዳው ላጣ ከስቃዩ ወርዶ፣

["እህ" በሉትማ
ተረዱት ያንን ሰው...
.
.
ፍቱን እሚፈውስ ባይገኝ እንኳ መላ፣
ሚያስታግስ ሚያስረሳ አሁንን ቡሀላ
ስጡት ያንሰራራ ምልሰት አይሁንበት፣
መራመድ ባይችልም መቆም ይሁንለት፣
መኖር እንዲያጓጓው ተስፋን አሽትቱበት፣
.
.
ቅን ልቡን ቢዘራ በችሎታው ቢያምን፣
ያን ግዜ ይቻላል ያለ ሰው ሰው መሆን።


@UniqueDy

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19