Get Mystery Box with random crypto!

#ሚወቀስ_ትዝታ . . ደንዳና ነው ልብሽ፤ ጀጋኝ ነሽ የኔ አለም! የወንዙ መደፍረስ፤ መገምሸር መደ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#ሚወቀስ_ትዝታ
.
.
ደንዳና ነው ልብሽ፤
ጀጋኝ ነሽ የኔ አለም!
የወንዙ መደፍረስ፤
መገምሸር መደርመስ፣
ሙላት መች አግዶሽ ዘልቀሽ ተሻግረሻል፣
"የኔ ነህ" 'ምትዪው፤
"የኔ ነሽ " የሚልሽ ሌላ አዳም ለምደሻል።
.
.
መልመዱንስ ልመጅ፤
ይቅናሽ አዲስ ጎጆ ፤
ይስመርለት ግብሩ ፍቅር ይሁን ዋልታው፣
የታመንሺው አምላክ፤
ምርቃት ያርግልሽ ጩኸትና ዋይታው።
.
.
ግና ለአንድ አፍታ ትዝ ባልኩሽ ሰሞን፣
ቀልቤን እንድገዛው አዘቦት እንዲሆን።
ፆሜን እንኳን ባልሽር፤
እንደው ላመል ያህል ትንሽ እንድል ዘና፣
ንግስናውን ካጣው፤
ገርጥቶ ከነጣው ከዘመመው ጎጆ ከቤቴ ነይና፣
አንሶላውን ውሰጅ፤
አልጋዬንም ውሰጅ፤
ትራሱንም ውሰጅ፤
"እፎይ" ልበል እስቲ ትላንቴን ልርሳበት፣
ትርፉ ማባከን ነው፤
አንቺን የሚያስታውስ መዓዛሽ ያለበት።


" ዐብይ " ( @abiye12 )

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19