Get Mystery Box with random crypto!

ወሩ መሥከረም ነው... ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እንጦጦ ማርያም... የ'መብርሐንን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ወሩ መሥከረም ነው...
ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር
እንጦጦ ማርያም...
የ'መብርሐንን ፣ በአሏን ለማክበር
ከክርስቲያኖች ቤት...
አርፍጄ እንደደረስሁ ፣ታቦት ወጥቶ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከታቦቱ አጠገብ...
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ካህኑ ይሰብካል
አንዳንዱ ምእመን ፣
ተአምር ያዘለ ..
ብጫቂ ወረቀት ፣ ለካህኑ ይልካል
ደግሞ ሌላ ተአምር...
ለካህኑ ጆሮ ፣ ዲያቆኑ ያንሻኩካል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካህኑ!
"ታ'ምር ነው ምእመናን ፣ አንድዜ እልል በሉ
አንኳኩ ይከፈታል ፣
ጠይቁ ይሰጣል ፣ ይላልና ቃሉ
"አፀደ ማርያም"
የተባለች እናት ፣ የማርያም ምስክር
ልጇን አስተምራ ፣ በስቃይ በችግር
ካንዱ ይንበርስቲ...
ተመርቆ ወጥቶ ፣ ያለ ሥራ ሲኖር
አምና በዚህ ሰዓት...
ከደጇ መጥቼ ፣ ተማፅኛት ነበር
ፀሎቴን ሰምታለች!
ልጄም ሥራ ይዞ ...
መቶ ዶላር ልኳል ፣ ካሜሪካን ሀገር፡፡"
እንዲህ እንዲያ እያለ
ስብከቱን አቋርጦ ፣ ተአምር ሲናገር...
በሴቶች እልልታ ፣ በወንዶች ጭብጨባ
የኢትዮጵያዊት ስለት...
ካሚሪካን ሀገር ፣ ተልኮ ሲገባ
ጥያቄ አምጣለሁ ፣ ዐይኔ እስኪያረግዝ እንባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አላለሁ...
ምንድነው እዚህ ሀገር ፣ ተምሮ መመረቅ?
እርግማን አይደል ወይ...
ሰው ሀገር ለመሥራት ፣ ተቸግሮ ማወቅ?
።፣፣፣፣፣።።።፣።፣፣
ምኑ ነው እውቀቱስ...
የተማሩት ነገር ፣ ላገር ካልጠቀመ
ምንስ ነው መቸገር....
ወድቀው ከፍ ያረጉት ፣ ሰው ሀገር ከቆመ?
ወይስ አልተቻለም...
እዚሁ ተምሮ ፣ እዚሁ ሀገር መስራት?
የተማረው ሁሉ...
ጥሏት ከነጎደ ፣
ማነው ይችን ሀገር ፣ የሚያስተዳድራት?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንድነው እማምላክ
የሠው ሀገር ገንዘብ ፣ የሰው ሀገር ፍራንክ
በእልልታ ታጅቦ ፣ ከደጅሽ ሚመጣ?
በማለት እያማጥኩ...
ጥያቄ እየወረድኩ ፣ ጥያቄ ስወጣ...
።።።።፣፣።።።።
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ የካህኑ ስብከት
ከታቦቱ ፊት ላይ....
"ተቃጠልኩኝ " የሚል
"አሰናብቺኝ " የሚል
በሰው ላይ ያደረ ፣ ያጋንንት ጩኸት
ከታቦቱ ዙርያ...
"አይኔ ነሽ ብርሃኔ
እመቤቴ ማርያም ፣ አብሶማ ለኔ"
እያለ ሚዘምር ፣ ክብ የሰራ ወጣት
ይህንን እያየሁ
ብዙ ጥያቄዎች ፣ ሳምጥ ሳጠራቅም
አንድ አይነ ስውር ሰው...
ፊቴ ተደቀነ ፣ ምፅዋት ሊለቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምነው እመብርሀን
ታደዪ ይመሥል...
አይኔ ነሽ እያለ
አብሶማ እያለ ፣ ወጣቱ ሲዘምር
ምን ይሰማው ይሆን...
ከደጅሽ የመጣ ፣ ምስኪን አይነስውር?
ስል እጠይቃለሁ ፣ ደግሞ እታዘባለሁ
ጥያቄ እያማጥሁ ፣ እንባ እወልዳለሁ፡፡
እዘኝ አዛኝቱ!
እዘኝ አዛኝቱ!!
እዘኝ አዛኝቱ!!!
በላይ በቀለ ወያ
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19