Get Mystery Box with random crypto!

የቱ ነው አዳምሽ? አይን ሲበዛብሽ የኔ ባይ ሲበዛ ራስሽን ብታይ አለምን እንደገዛ ለምርጫ ቢከብድሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የቱ ነው አዳምሽ?
አይን ሲበዛብሽ የኔ ባይ ሲበዛ
ራስሽን ብታይ አለምን እንደገዛ
ለምርጫ ቢከብድሽ የቱን እንደምትይ
ሌላው ትርፍ ነው ልብሽን ተከተይ
እንደ ጽጌሬዳ ሁሉም ቀጣፊሽ ነው
አበባ እንዳየ ንብ ከባቢሽ ብዙ ነው
ግን አስተውይና ንብሽን ምርጪ
ለየትኛው ንብ ነው ራስሽን ምትሰጪ
ለውበትሽ ወድቆ ለመልክሽ ሰጋጁ
እሱ ቅርብ ሂያጅ ነው ፍቅር የለም በእጁ
አንቺነትሽን ብሎ ለፍቅር የመጣው
እሱ ነው ቀሳሚሽ በቶሎ ምረጪው።


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19