Get Mystery Box with random crypto!

#ልክ_ነው_ያነሰሽ አንቺኮ የዋህ ነሽ አንቺኮ ፍቅር ነሽ አንቺኮ ቆንጆ ነሽ አንቺኮ ውድ ነሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#ልክ_ነው_ያነሰሽ

አንቺኮ የዋህ ነሽ
አንቺኮ ፍቅር ነሽ
አንቺኮ ቆንጆ ነሽ
አንቺኮ ውድ ነሽ
አንቺኮ እንዲ ነሽ
አንቺኮ እንዲያ ነሽ ብዬ ብነግርሽም
እውነት አይመስልሽም
ቀን ከሌት ብነግርሽ የማፍቀሬን መጠን
ቀን ከሌት ብነግርሽ የራስሽን መጠን
ውሸት ነው ሚመስልሽ እውነት ላይ መሰልጠን
ግን
ውሸት ባቶጂ እንኳን መስማት ካሰፈልገሽ
ነሽ ያልኩት በሙሉ ልክ ነው ያነሰሽ
መሆን ላይመጥንሽ
እውነት ላይወጥንሽ
ላወድስሽ ስጥር ላልችል ተቋቁሜ
እራሴን አገዘፍኩ ባንቺ ልክ አቁሜ
(እዳ)

እራስን ሳይችሉ
አንቺን ለማወደስ በትንሹ መጣር
ወደሞት አዝግሞ ለህይወት ማጣጣር
ካለመቻል በላይ ተጉዢያለሁ ብዙ
ይቅርብኝ ከእንግዲ ከአቅሜ አልታበይ
የውሸት መነሻ እውነት ስለሆነ
ውሸቴን በሙሉ አምነሽኝ ተቀበይ
ምንናልባት የዛኔ
ምናልባት ያን'ለት
መጀመሪያ ይሆናል መጨረሻ ማለት

አዲብ
( @Tufaw_muhe )