Get Mystery Box with random crypto!

እመጣለሁ ብለህ ትመጣለህ ብዬ ድንኳን ባደኩንም ንፍሮ ባስቀቅልም ምስር ባስለቅምም ጥቁር አገል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እመጣለሁ ብለህ

ትመጣለህ ብዬ ድንኳን ባደኩንም
ንፍሮ ባስቀቅልም
ምስር ባስለቅምም
ጥቁር አገልድሜ አስለቃሽ ብቀጥርም

አንተ ግን ቀርተሀል ዛሬም እንደ ድሮ
ከልቤ ለመሞት ከያዝከዉ ቀጠሮ።

ገዳይ ሰዉ አላዉቅም............

ሟቹም ወንጀለኛዉ ከሳሹም ፈራጁም
አንተዉ ራስህ ሆነህ ከችሎት ቆመሀል
መከራከር አላዉቅ አሁን ምን ይባላል።

ና ላንጎራጉርልህ.............

ለአርባና ሰልስትህ አልተዉሽም ብሎ ጥሎኝ ሄደ ብዬ ሰዉ ላስለቅስልህ
ጋሻ ነበር ብዬ ጦር ላሰብቅልህ።

ና እስቲ አንዴ ሙትልኝ..........

ከአፈር ተደባለቅ
ስጋህን ብል ይብላዉ አይኔ እያየህ እለቅ።

የኮራህበት ገላህ ይፈራርስ አለሜ
እኔም ገለሞተች ልባል ገደምዳሜ።

ና እስቲ ወጉ ይድረስህ...........

ሟችነት ይሻላል
በቁምህ ከመሞት በመቃብር ያምራል።

ና እስቲ አንዴ ሙትልኝ.............

እኔም እርሜን ላዉጣ
ትቶኝ ሄዶ ሳይሆን
ሞቶ ነዉ እያልኩኝ አስሬ ልቀጣ።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@TIZITA21

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19