Get Mystery Box with random crypto!

#እያስታወስኩ ልርሳህ (ረድኤት ሰኢድ መሀመድ) . . ማስታወስ ህመም ነው መርሳትም ስቃይ ነው ሁሉ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#እያስታወስኩ ልርሳህ
(ረድኤት ሰኢድ መሀመድ)
.
.
ማስታወስ ህመም ነው
መርሳትም ስቃይ ነው ሁሉም ለየብቻ:
ጋላቢ ሆነው ሳሉ
ከመኖር ጀርባ ላይደሞ ያለኮርቻ
(መኖር ሲቆስልም አይደል እኛ የምንደማ?!)
ትርፉ መገሽለጥ ነው ዳሩ መቆሳሰል
ኖረው ላይኖሩበት
በናፍቆት መብሰልሰል:
በትዝታ መብሰል
በነበር ላይ መክሰል።

እኔማ አስቤ ልረሳህ ወስኜ
ወሽመጤን ስበጥስ ልቤ እየተጣላኝ:
ብሩሻም ትዝታህ
ሀረግህን ሲጥል እኔው እኔን ጠላኝ።
(ፍርጃ ነው!)

እኔ እርጥብ ሬሳ
ያልደረኩ ያልፈረስኩ ያልከሳው:
አንዴ ሳመኝና
በትንፋሽህ ልዳን መኖሬን መልሰው።
ልልህ አስብና
ሀሳብ አቀናና
ደሞ ተወዋለሁ 'ረሳሁህና።

ማስታወስ ህመም ነው
መርሳትም ስቃይ ነው ሁሉም ለየብቻ:
እየተጋለበ
ከመኖር ጀርባ ላይ ደሞ ያለኮርቻ:
ትርፉ መገሽለጥ ነው
ዳሩ መቆሳሰል
ኖረው ላይኖሩበት
በናፍቆት መብሰልሰል
በትዝታ መብሰል
በነበር ላይ መክሰል።

ከጠቆረው ልቤ
የቀላብኝ ገፅህ ውል ውል እያለ ጠፍ ልቤን ያረካል:
መርሳቴ አፈር ለብሶ ትውስታህ ይፈካል።
አንዱን ያማል ማማጥ
አንዱንያማል መምረጥ
እልም ብሎ መኖር እልም ብሎ መሞትእኔስ አይጣፍጠኝ
ይጥማል መዳኔ ይጥማል አበሳህ:
እየዳንኩኝ ልሙት
ልሙት እየዳንኩኝ እያስታወስኩ ልርሳህ!¡


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19