Get Mystery Box with random crypto!

ፀጋዬ ገ/መድህን [ ሕይወት ቢራቢሮ ] . በይ ብር በይ ቢራ ቢሮ፣ ክረምት ላንቺ ብቻ አለፈ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ፀጋዬ ገ/መድህን

[ ሕይወት ቢራቢሮ ]
.
በይ ብር በይ ቢራ ቢሮ፣ ክረምት ላንቺ
ብቻ አለፈ
ሌላው በጎርፍ ጎረፈ
ሞተ፣ በተኛበት ረጋ…
ፀደይ ላንቺ ብቻ ነጋ
ሽር ብለሽ መንቆጥቆጥ ነው፤ ከዚያም፤
ከዚያም፤ ከዚያም ሰምሮ
አወቅሁብሽ፤ ነቃሁብሽ፤ አንቺ ሕይወት
ቢራ ቢሮ…
ቀናሁ መሰል አንች ወላዋይ?
ነይ ብር በይ እንወያይ
አንቺ የዕፅዋት አዋዋይ
ከፀደይ ጋር ፀደይ መሳይ
ከአበባም አበባ መሳይ…
ምን አለበት ላንዲት ሰሞን
ቢራ ቢሮ እኔ አንቺን ብሆን?


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19