🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ያ'ምላክ [ቶማስ ትግስቱ] . . እና እኔ እና አንቺ እንስሳት እፅዋት አዋፋት እና አምላክ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ያ'ምላክ

[ቶማስ ትግስቱ]
.
.
እና እኔ
እና አንቺ
እንስሳት
እፅዋት
አዋፋት
እና አምላክ
።።።።።።።።።።።።።።
ከለታት አርብ ነው
ቀና ስል ጣሪያ አለ
ጭልጭል የሚል መብራት
ከሆዱ ያዘለ
መሃል ላይ አይመስልም
ዳርም ላይ አይደለም
ግን ደግሞ ተበስቷል
ወዲያ ጥግ ጥጉን
ሸረሪት ተኝቷል
(ከሸረሪቷ ጋር)
ብዙ ዝምባ ዝቦች
ቢምባ ቢምቦች
ትንኛ ትንኞች
ይተራረባሉ
ዝዝ ብዝ ጥዝ ምናምን እያሉ

(እኔስ?)
እኔ
ደክሞታል ወገቤ
አሞታል እራሴ
አላውቅም ጠግቤ
በስብሷል ትራሴ
ጀርባዬ ተኝቷል
እግሬም ተዘርግቷል
አጭር ነው ቁመቴ
አልጋው እረዝሞታል
ቀጭን ሰውነቴ
አልጋው ግን ጠቦታል
(እናም አልጋ ላይ ነኝ)

ግን አልጋው ጠቦኛል
አጥብቆ ገርሞኛል
(ማታ የጠጣሁት አለቀቀኝ ይሆን?)
አምቡላው
አተላው
ቅራሪው
(ዝቃጫም መጠጡ )
ሲደመር አስካሪው?
አይ አይ ለቆኛል
በርግጥም ጠቦኛል
ደግሞ በግራ ጎን
(በቀኝ ግርግዳ ነው)
ዳሰስኩ ጥግጥጓን

ሴት

አውዝቢላሂ ወ መንፈስ ቅዱስ
ማናባቷን ነው እጄ ሚዳብስ?

ግራ ጎኔ ጋር ሴት
ሊያውም እኔ ቤት
እኮ ማን ጠርቷት?
እኮ ማን ጋብዟት?
ደገምኩ ዳሰስኳት

ብዥ ይላል ጣሪያው
ማታን ሲያሳየኝ
ጥምብዝዝ ብዬ
እሷ ግን አዝላኝ
ከቤቴ ገብታ
ካልጋ ስጥለኝ
ልብስ አወላልቀን
ስላት ስትለኝ....

ሸረሪቷ እና....
ዝምባ ዝምቦቹ ፣
ቢምባ ቢምቦቹ ፣
ትንኛ ትንኞች
ይፋፌዛሉ
ይሳሳቃሉ
ዝዝ ብዝ ጥዝ ምናምን እያሉ
(<ድንቄም ባለ ሴት> ነገር)

ዞሬ አየሁሽ፤
ወፍራም ሰውነት
የ ቀይ ዳማ ፊት
ቡግራ ቡግር
ነጭና ጥቁር
ድብልቅ ጸጉር
ሽልጦ ከንፈር (የምር ትልቅ ነው)
ሌላውስ ይቅር

ሰው የጠላው እኔን
ያቀፈ ሰውነት
የሳመ ሴትነት
የሾመ አዳምነት

ሔዋኔ
ሔ....ዋ....ኔ
ሔ.....ዋ...... ኔ....ነሽ
በግራ ጎኔ አምላክ ያኖረሽ
እሱ የጠራሽ
እሱ የጋበዘሽ

ሰካራም
እድፋም
ቱሃናም
ፎከታም
ብሆንም
በስካር እንቅልፍ አምላክ ያመጣሽ
ካጥንቴ አጉሎ ላንቺ የሰጠሽ።
(እኔ ቀጭን እሷ ወፍራምም አይደለን?)

"ሄዋኔ ስሚኝ"
አንቺ እስካለሽኝ
አንቺ እስከኖርሽኝ
ፀሃይ አጠልቅም
ሃጣን አይወድቅም
ፃድቅ አይፀድቅም
ዝምብ አትስቅም
ቢምቢ አትንቅም
ትንኝ አላውቅም

አ..ላ..ው..ቅ...ም አላውቅም(34×)
ማንንም አላቅም

ድሮም ባ'ዳም አለም
ሄዋን እና እሱ እንጂ
የሰው ፍጡር የለም

እናም በዚች ምድር፤
እንስሳት
እፅዋት
አዋፋት
እና አምላክ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እና እኔ
እና አንቺ
ብቻ እንቅር ፍቅር

[ቶማስ ትግስቱ]

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19