🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የቱ ጋር ልተኩስ ጥፍርህ ጋር........... ጥፍርሽ ነዉ የማረከኝ ብለህ እንዳቀረብከኝ ከእ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የቱ ጋር ልተኩስ

ጥፍርህ ጋር...........

ጥፍርሽ ነዉ የማረከኝ
ብለህ እንዳቀረብከኝ
ከእግርህ ጋር አድርጌ
ጧ ላርገህ ................

አይንህ ይሻለኛል
በመዉደድ አስታኮ
ስልምልም እያለ
ልቤን ያታለለ
ሞጭላፋ ዘራፊ
እሱነዉ ቀጣፊ።

እንደዉም ከንፈርህ
ጥርስና ምላስህ
ሳቅና ቃላትህ

እሱ ደሞ አይሆንም
ንግግር በጥይት ሲሞት ታይቶ አያቅም

እጅህ ጋር.........
እየደባበሰ ገነት ያደረሰ
አዉራ ጣት፣ ሌባ ጣት፣መሀል፣ ቀለበቱ
የቱን ልሹትልህ ምረጥ ከአራቱ

ለማርያሟ ጣትህ እድል እሰጣለሁ
እንታረቅና እርቅ ይዉረድ እላለሁ።

እሱ ካልሆነ ግን እመነኝ አለሜ እ..ተ..ኩ..ሰ..ዋ..ለ..ሁ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19