Get Mystery Box with random crypto!

ስንኞች (በእውቀቱ ስዪም) በብዙ ጭንቅና በብዙ መከራ አቁሜ ሲጃራ እጠነቀቅ ብየ፤ ለሳምባ ለልቤ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ስንኞች
(በእውቀቱ ስዪም)

በብዙ ጭንቅና በብዙ መከራ
አቁሜ ሲጃራ
እጠነቀቅ ብየ፤ ለሳምባ ለልቤ
በትምባሆ ምትክ ፤ንፉግ አየር ስቤ
ከሱስ ጸዳሁ ልበል?
መኖርን የሚያክል፤ ሱስ ተከናንቤ

ከገነት ጋር ጠፍቶ ፤የጤና ትርጉሙ
የተሻለው ሕመም፤ ጤንነት ነው ስሙ፡፡

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19