Get Mystery Box with random crypto!

[አትፈርስም] ትፈርሳለች ይላል ሀገር እንደትዳር በሰከረ ቁጥር ጥሏት እንደሚያድር ትፈርሳለች ይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

[አትፈርስም]

ትፈርሳለች ይላል
ሀገር እንደትዳር
በሰከረ ቁጥር
ጥሏት እንደሚያድር
ትፈርሳለች ይላል
እንደጨረቃ ቤት
በጨለማ ሽፋን
በሩጫ እንደሰራት
ትፈርሳለች አትበል
በጽኑ ሐይማኖት
በቃልኪዳን ማገር
የተመሠረተች
የታነፀች ሀገር
ትፈርሳለች አትበል
ኢትዮጵያ አትፈርስም
ንፋሱን ቢያስነሳ
ቸነፈር ቢያመጣም
እድፏን ሊያጠራ እንጅ
ሊያፈርሳት አይደለም።

ብርሃኑ ዘላለም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19