Get Mystery Box with random crypto!

ሔለን ፋንታሁን ምንም .... የታመመው እግሬ መርገጫውን ያጣ ተንከራታች ዓይኔ የሚያርፍበት ያ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሔለን ፋንታሁን

ምንም ....

የታመመው እግሬ መርገጫውን ያጣ
ተንከራታች ዓይኔ የሚያርፍበት ያጣ
የሚባዝን ልቤ መግቢ ጎጆ ያጣ

ምኑ ነው መስከረም
ምኑ ያደይ መልኩ ?
የቱ ነው የነጋ
የብርሃን ልኩ ?
የታል ?
የለም ! የለም !
ሐምሌ ላይ ለቆመ
ተላምዶ ከፅልመት
ቀን ላልቆጠረ ሰው
መች ሊሞላ ዓመት
መቁጠር የቱን ግዜ ?
ማለፍ የቱን መዓት ?
የመኖር ትርጉሙ
የመሞትስ ንግርት ?
የታል ?
የለም! የለም !
ቀን ያላስተማረው የመቁጠሪያን ቀመር
ምንም ነው መለኪያው ለምንም ላይ ስፍር ::

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19