Get Mystery Box with random crypto!

ትመጫለሽ ብዬ ልቤ ደጅ አደረ ትዝታዬን ይዤ ሀሞቴን መክሬ ለልብሽ ታዝዤ ....... ትመጫለ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ትመጫለሽ ብዬ


ልቤ ደጅ አደረ
ትዝታዬን ይዤ
ሀሞቴን መክሬ
ለልብሽ ታዝዤ
.......
ትመጫለሽ ብዬ
........
ሌላ ሴት እንዳላይ
አይኖቼን አጥፍቼ
ልጎምእንደሌለዉ
ምላሴን ዘግቼ
........
ትመጫለሽ ብዬ
.........
አለሌዉ እግሮቼን
በስለት ወግቼ
አፍሮ ጎፈሬን
በምላጭ ላጭቼ
.........
ትመጫለሽ ብዬ
........
ደረቴን አጥብቤ
ከንፈሬን አቁስዬ
ሰልካካ አፍንጫዬን
በመላ አስነቅዬ
..........
ትመጫለሽ ብዬ
.......
ቤቴ ክፍት አደረ
ማጀቱ አደራ
አዉሬ ረግጦት ሄደ
እየተወባራ
........
ትመጫለሽ ብዬ
........
እዉር ደንባራዬን
ቁስሌን አላከምኩም
ደረቴም አልሰፍም
ፍቅር አልጀመርኩም
.........
ትመጫለሽ ብዬ
........
እቴ አልቦዘንኩም
ሁሌ ከማደሪያሽ
እጠብቅሻለሁ
ብልም እንዳይበላሽ
.......
ትመጫለሽ ብዬ
..........
አንድ ቀን ፈጣሪ
ቢመልስሽ ብዬ
ተሳስቶ ይሆን
እያልኩ ተታልዬ
........
ትመጫለሽ ብዬ
.........
ለካ አንቺ ቀርተሻል
ካፈር ተዋህደሽ
ከብል ተስማምተሻል
.......
ትመጫለሽ ብዬ
......
ዛሬ አልጠብቅሽም
ለካ እኔ እንጂ
አንቺ ወደኔ አትመጪም።
በፊፊ የተጻፈ

ቅኔ ራስ ግጥም

ይሄን ግጥም ስሜት
በሚነካ መልኩ ገጣሚ
ወይም አንባቢ ወንዶች
voice lakulgn
@feyameta

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19