Get Mystery Box with random crypto!

አንተዬ አንተእኮ አታፍርም ይሄኔ ረሳሀኝ አንተኮ ደፋር ነህ ከሌላጋ ሆና ብለህ ጠረጠርከኝ መቼ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንተዬ

አንተእኮ አታፍርም ይሄኔ ረሳሀኝ
አንተኮ ደፋር ነህ ከሌላጋ ሆና ብለህ ጠረጠርከኝ

መቼ ያልቅብህና............

ዘንግታኝ ይሆናል ብለህ ስለገመትክ
ሌላዋን ለምደሀል
ያለፈ ፍቅሬን ልክ እንዳረጀ እቃ አዉጥተህ ጥለሀል

ባክህ መልስልኝ......

ልዋጭ ልሁንና ያሻህን ልቀይር
ወይ ቁራሌ ሆኜ በብር ልተምን

እንደ ቅራቅንቦ
ባለቤት እንዳጣ
ጥቅም እንደሌለዉ
እንደ ጠላት ገንዘብ
መዉደዴን አራክሰህ
ባክህ አትጣልብኝ ያፍቃሪህን ዋጋ::


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19