Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ሀገር በ አቤል ዮሐንስ ከየት ልጀምር መሰለህ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የኛ ሀገር
በ አቤል ዮሐንስ
ከየት ልጀምር መሰለህ
የኛ ሀገር ኮብል፤ አስፋልቱን ያስንቃል
ለአያንህ ውብ ቢመስልም፤ እግርህ ግን ይሰጋል
በጉልበትህ ሰርተህ ፤የሰራኸው መንገድ፤ ጉልበትክን ከደፋው
ሌላ የትም የለህ ፤እኛ አገር ነው ያለኸው

መብራታችን ደግሞ ፤ዲም ላይትን ያስንቃል
ከኗሪ ቤት ይልቅ ፤ፓሪ ቤት ያደምቃል
ይህን በማስመልከት
በአዲስአበባ ፤ከአፅናፍ እስካፅናፍ ፤ጭፈራ ቤት ሞልቷል
ጭፈራ ቤት ገብተህ ፤ዲጄው ብቻ ከሆነ
የጄኔነተሩን ፤ገመድ ሚጠቀመው
ወዳጄ
እዚው ከኛ ጋራ ፤እኛ ሀገር ነው ያለኸው

በቲቪህ መስኮት ላይ ፤ፏፏቴ እያየህ
ቧቧህን ስትከፍተው ፤ጠብታ ከሌለህ
ሁለት ኩባያ እንኳ ፤ በቀን ያልጠገበች፤ አንጀት ይዘህ ሳለ
ሁለት መቶ ሚያህል ፤የውሀ ፋብሪካ ፤በመኖሪያህ ካለ
ከኛ ሀገር ውጪ ፤እንዲህ ያለ ታሪክ ፤ከወዴት ታያለህ

በጤና ጣቢያችን ፤ሄደህ ስትታከም
ሆስፒታል ክሊኒክ ፤ሁሉ ትጠላለህ
እንደ ቤቲንግ ጌም ፤በግምት መርምረው ፤መርፌ ቢሰጡህም
ሀሳብ እንዳይገባህ ፤አንዱም ግምታቸው ፤እውነት ሆኖ አያውቅም
እንዲ አይነት ዶክተሮች ፤ያሉበት ጋር ካለህ ፤ከኛ ሀገር አይዘልም

ደግሞ ከታክሲ ላይ ፤አስር ብቻ ሁናቹ
ለአስራ ሁለት ወንበር ፤ከተመታታቹ
ለሶስት ብር መንገድ ፤ቡጢና እርግጫ ፤ከተቃመሳቹ
ወይ ደግሞ በባስ ውስጥ ፤የያዝከውን ወንበር
ለአዛውንት ብለህ ፤ስትቆም በእግር
ከምርቃት ይልቅ ፤ወንበር ከናፈቀህ
ወዳጄ ወዳጄ ፤ከኛ ሀገር ውጪ ፤ወዴት ትሆናለህ

አንድ የመጨረሻ

መኖር ከሌለብህ ፤ሰፈር ዉስጥ ተገኝተህ
ከስራ ፈት ወጣት ፤ስብሰባቸው መሐል ፤አይናቸው አርፎብህ
ድንገት ዞር ስትል ፤ለምን አየኝ ብሎ
ድድህን ከመንጋጋህ ፤ካደባለቀልህ
ከኛ ሀገር ውጪ ፤የት አባ ቶናለህ

ፈጣሪ ይሁንልህ

@abelyohannes12

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19