Get Mystery Box with random crypto!

በምቀኛ ሃገር ገና ባያመቴ በሁለት አስርቱ እንደመቶ ሜትር እንዳጭር ርቀቱ መንገዱን ፉት ብሎት አ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በምቀኛ ሃገር

ገና ባያመቴ በሁለት አስርቱ
እንደመቶ ሜትር እንዳጭር ርቀቱ
መንገዱን ፉት ብሎት
አፈትልኮ እንደቮልት
ሽቅብ ታቹን ይዞ ሮጦ ተግደርድሮ
ደሞ እንደጄትሊ ዘሎ ተስፈንጥሮ
ያ የኔ አበባ
ከኪሴ ሊገባ
ትንሽ ሜትር ብቻ ፣ የቀረው ዘንድሮ
የቡዶቹ ሲሳይ ፣ ፀጉሬ ሚናሮ።

ጠንካራ እንደሽቦ ቧጣጭ እንደቆርኪ
የኔ ፀጉር ሉጫ የልጃቸው ኪንኪ፤
ይህንን ልዩነት ይመለከቱና
የጓደኛዬ እናት ወይዘሮ ባፈና
እና
ስማቸውን ቄስ አብሮ ይጥራውና...
ጎረቤት ተብዬ ወይዘሮም ስንዱ
በቅናት ቢጨሱ ቢበግኑ ቢነዱ
"ሉጫ ፀጉር ለሴት ፥ ምን ሊበጅ ለወንዱ"
እያሉ አውርተው በየዳር መንገዱ
አስበሉት ፀጉሬን ወይ ራሳቸው በሉት
እንደተራሮቹ
ራስ ቅሌን አሯቅተው ባዶውን አስቀሩት።

መልኬ እንኳን ባያምር ቢወርሰው ቋቁቻ
እንደሙሴ በትር በፀጉሬ ብቻ
ብፈልግ በዘኒት በቁሙ ፈርዤው
ሲያሻኝ አበጥሬ ቁልቁል አስተኝቼው
መድረኩን ሳልመራ
ከነብያት መሃል ስሜን ሳላስጠራ
ሳልሆን አባወራ...

ወይም አንዷን ቆንጆ ፣ የሰፈሬን ጉብል
አንድም ቃል ሳይወጣኝ ፣ ምንም ነገር ሳልል
በዞማዬ ብቻ ፣ ቀልቧን አማልዬ
ከጎረምሶች መሃል ፣ ሳልወስዳት አስጥዬ...

ባለንጋ ጣቶቿ ፣ እየዳበሰችኝ
ከማላውቀው አለም ፣ እየወሰደችኝ
ነቃው ስል ደጋግማ ፣ ጠልፋ እየጣለችኝ
በአስማቷ ምትሃት ፣ ሳታስለመልመኝ...

ከጭኖቿ መሃል ፣ ወገቤን አስምጣ
ልቤን እንደቂቤ ፣ ሳተወው አቅልጣ
እኔም እንደሴፉ ፣ ልሆንነው መላጣ።

ሰው በመሆን ቅጡ ፣ በተፈጥሮ እዳ
በምቀኛ ሃገር ፣ በሞላበት ቡዳ
በስምንተኛው ሺ ፣ በተፋለጥ ዘመን
የሳሱለት ቀርቶ ፣ ቸል ያሉትስ ቢሆን
እንኳን ለዘመናት ፣ መች ያድራል ላንድቀን።

"ቮልት" = ጀማይካዊው የመቶ ሜትር ሯጭ
"ጄትሊ" = ቻይናዊው ካራቴቲስት አክተር

ልዑልሰገድ ኪዳኔ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19