Get Mystery Box with random crypto!

በድሮ ዘመን ነው አሉ(እድሜ በሽ በሆነበት ዘመን) ልጅየው ወደ 130 አመት ምናምን ይሆነዋል እና | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በድሮ ዘመን ነው አሉ(እድሜ በሽ በሆነበት ዘመን) ልጅየው ወደ 130 አመት ምናምን ይሆነዋል እናቱ ደግሞ 165 አመት ይሆናቸዋል እና ልጃቸው በድንገት ይሞታል ከዛ እናትየው ሲያለቅሱ "ምነው ልጄን ባጭሩ ቀጨኸው" እያሉ ምርር ብለው አልቅሰዋል ይባላል።

ዘመን ሲገለበጥ

ሺ አመት ያኑርህ የሚለው ምርቃት
በዘንድሮ ትርጉም በጉልህ ሲገልፃት
እያረሩ ኑሮ ኦየተኙ ንቃት
ብለው ያሰፍሯታል
እርግማን አረገዋት

ታዲያ...ሺህን የሚያህል ኑሮ
ብዙ አመታትን
ብዙ ዘመናትን ደርድሮ
ሺ አመት ያኑርህ ብለው ቢመርቁት
አሜን ባይ አይደለም
ስድብ ነው ሚያተርፉት

ህይወት ያልጀመረ መኖር ያለመደ
የማቱሳላ አድሜን መያዝ ያልወደደ
በሰበብ አስባቡ ሞቴን ሞቴን ካለ
የሺህ እድሜ ምርቃት እንዲ ከቀለለ
በቶሎ ይቅጠፍህ መባሉ አይቀርም
ለሞት ናፋቂ ዘመን ይሄኛው አያንስም

የዘንድሮ ፀሎት...
እግዜሩን አጥብቆ አብዝቶ ይጠይቃል
ህይወት ያልጀመረ ሁሉ ሞትን ይናፍቃል

ዮኒ
ኣታን

@yonatoz


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19