Get Mystery Box with random crypto!

መቼ ነው ሚፈታ!? ቀመር ተለውጦ ፣ ሲሄድ መንገድ ዞሬ ስጋዬን ቀልቤው ፣ ለሰው በላው አውሬ እን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

መቼ ነው ሚፈታ!?

ቀመር ተለውጦ ፣ ሲሄድ መንገድ ዞሬ
ስጋዬን ቀልቤው ፣ ለሰው በላው አውሬ
እንደ ፎቅ መስታወት ፣ ፊቱ አቅለጥልጦ
የኔን ወዝ ደቅኖ ፣ እንደሸንኮር መጦ
የሱ የደም ግባት ፣ ወዘናው አማረ
ኪሎዬን ቀንሶ ፣ ኪሎውን ጨመረ።
*************

ልክ እንደ ቀይ ባህር ፣ የየብስ ላይ ስፋት
ልክ እንደ ሰሃራ ፣ የሰማይ ስር እሳት
ልክ እንደ ራስደጀን ፣ የመሬት ከፍታ
ልክ እንደ ሚችገን ፣ የምድር ዝቅታ
ፋፍቶ ቢጠበድል
ረዝሞ ቢንቀዋለል
ቢወጠር ቢያስካካ
'ማን ሊነካኝ!' ብሎ ፣ ከግዜር ቢለካካ !!
ስንቱን በጉያዋ ፣ አፍና እንዳሊያዘች
ዛሬስ ከብዷት ኖሮ ፣ ምድሪቷም ቃተተች።
*******************

ታዲያ
እኮ ታዲያ!!
ሰሚ ሸንጎ የለሽ ፣ እኔዋ አህያ
ያው እንደጣለብኝ
እንጀፈረደብኝ ፣ ብቻዬን አውላላ
የጫነብኝ ቀንበር ፣ ማነቆው ሳይላላ
የዚን ጥንብ መዓት
ሸክም ተሸክሜ ፣ ዝንት አለም ልኖርነው !?
ወይስ ደግሞ ዳግም
አንድ ቀን ቀን ወቶ
ያመታት ሸክሜን ፣ አስኪፈታልኝነው !?
**************************
(ከመሠለ ከልካይ) መጋቢት ፳፻፲፫ ዓ.ም
ቴክሳስ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19