Get Mystery Box with random crypto!

ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህፃን በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህፃን

በደብተርሽ ምትክ
ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ
ካልፎሂያጅ እግር ስር፤
እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ
ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ አንጋጠሽ ወደ ላይ
ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ
ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው
ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው !!
አፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ
መስኩ ከነጎርፉ ፥
ሰማይ ከነዶፉ ፥ ለጌቶች ተሽጦ
አተር ነው እያሉ፤ አፈር ዘግኖ መፍጨት
ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት
ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት
ይህንን ማን ሰጦሽ
ገና በልጅነት፤ ልጅነት አምልጦሽ፡፡
በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ
በክራር ተማግሮ
በቆመ ከተማ
እምባሽ ቅኝት የለው ፤ ለሰው አይሰማ፡
ጠዋት የፎከረ ፤ ቀትር ላይ ሲረታ
ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ ትናንት የበረታ
ኑሮን ያህል ሸክም ፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡
ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡

በእውቀቱ ስዩም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19