Get Mystery Box with random crypto!

… እምቢ ለሃገሬ … ምን አጠፋ ጋራው ምን በደለ ወንዙ!? ሴፉን ያስመዘዘው፣ እብሪት ነው ጦሰ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

… እምቢ ለሃገሬ …

ምን አጠፋ ጋራው ምን በደለ ወንዙ!?
ሴፉን ያስመዘዘው፣
እብሪት ነው ጦሰኛው ጥጋብ ነው መዘዙ።

ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ…

ቁጣው የነብር ፥ ግርማው ያምበሳ
መካች የሌለው ፥ ቆርጦ ሲነሳ፤
ሃሞቱ ሙሉ ፥ ልቡ የኮራ
ጠላት ሰባሪ ፥ ባንዲት ስንዘራ፤
ደሙ ኩምጡ ፥ ገፁ የነቃ
ለናት ሃገሩ ፥ ቋሚ ጠበቃ።

ዘራፍ አካኪ ዘራፍ… (×2)
ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ…

ገና ከድሮው ፥ ገና ከጥንቱ
ያባቶቼ ነው ፥ አርበኝነቱ፤
ታሪኬን ረስቶ ፥ እኔን ባይፈራ
እሰጠዋለው ፥ አይኑን ላሞራ፤
ወሰኔን አልፎ ፥ ቢገኝ ከደጄ
እሰብረዋው ፥ አጥንቱን በጄ፤

ክንዴ ነበልባል ፥ መዳፌም እሳት
ያስከፉኝ ጊዜ ፥ የተቆጣው ለት
ለወደድኩትም
አልመለስም ፥ እንኳን ለጠላት።

ዘራፍ ጎበዝ ፥ ዘራፍ ጀግናው
ያባቱ ልጅ ፥ የሳተናው
ዘራፍ ጎበዝ ፥ ዘራፍ ወንዱ
የሳቱ ልጅ ፥ ያርበድብዱ።

እንኳን በወሬው ፥ ልርድ ልሰጋ
ባካል ቢመጣም ፥ እኔን ፍለጋ
እወጋዋለው ፥ በጦር ጋሻዬ
እቆርጠዋለው ፥ በጎራዴዬ
ቢያቅተኝ እኳን ፥ አለ በሬዬ
አይጠመድም ፥ ለዛ ወመኔ
አይታዘዝም ፥ በጭራሽ ለሱ
ይገለበጣል ፥ እንደ ጉሊሱ
ይከሰከሳል ፥ እንደ ጠርሙሱ።

ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ…
ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ… ዘራፍ…

(መሰለ ከልካይ)
ከ"ታጋቾቹ" የተቀነጨበ።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19