Get Mystery Box with random crypto!

ትችይበታለሽ አቤል ዩሐንስ ትችይበታለሽ እለት ተእለት ላይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ትችይበታለሽ
አቤል ዩሐንስ
ትችይበታለሽ
እለት ተእለት ላይ ቁንጅና መጨመር
የራቀሽን ሁሉ በትዝታ ማሰር
እንደጋለሞታ ዓይንሽ ማሳመር

ትችይበታለሽ
ከእብደት ገበያ ገላሽን መቸብቸብ
ኪስሽ እንደሞላ ክብርሽን መሰብሰብ
ባለቤት ለማጥመድ ስራሽን ማራቀቅ
ከውርጩ ገላሽ ውስጥ
ሞቃት ቃላት ማፍለቅ

ትችይበታለሽ
ክፉ ክፉን ሁሉ ትኖሪበታለሽ
እኔ በበኩሌ አነድ እውነት ልንገርሽ

ከእለታት አድቀን ልክ እንደ ብርሌ
በዳሌሽ እያሰብሽ ጭንቅላትሽ ጠቦ
ሁሉም ሲጨርስሽ ከጠጅሽ ጠትቶ
የሰከረ ለታ ጥሎ ይሰብርሻል
የቻልሻቸው ሁሉ ያኔ ያቅቱሻል



ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19