Get Mystery Box with random crypto!

የሰማይ ቤት ግሮሰሪ (በላይ በቀለ ወያ) . . ጨረቃ' ምንላት ግሮሰሪ ቤት ናት 'ሰማይ' ለምንለው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የሰማይ ቤት ግሮሰሪ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
።።።።
ከዋክብት ደግሞ ፣ አብረዋት 'ሚወጡ
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋር ሚጠጡ!!!
።።።
በጣም የሰከረው...
ራሱን ከሰማይ ፣ ፈጥፍጦ ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ፣ ማለት ነው የኛ እድል!!!

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19