Get Mystery Box with random crypto!

ተመስገን (ሚካኤል .አ) ለውሀ ቢቀረጥ ለማየት ቢከፈል ለጠሀይ ቢቆጠብ አየር ቢከለከል ለመስማት ቢ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ተመስገን
(ሚካኤል .አ)
ለውሀ ቢቀረጥ ለማየት ቢከፈል
ለጠሀይ ቢቆጠብ አየር ቢከለከል
ለመስማት ቢያስጨንቅ ለማሽተት ቢቀጣ
አቤት የእኛ እጣ!
ዋጋ ቢወጣለት እያወሩ መስማት
በደረሰኝ ቢሆን መራመድ መተኛት
እግዚኦ የኮመቴው የህግ አውጭው መዓት!
ይህን ሳይ ብቻ ነው ወደ ላይ ማንጋጥጥ
የዓለም ማጣቴን ... በስድብ የማለውጥ
ውድ መነፅር ሳጣ ከጎኔ ማተርኩኝ
መኪና አልባ ስሆን አቀርቅሬ አየሁኝ
ማየት የተሳነው እግር አልባም አለ
እንዴት ብዬ ላማር ሁሉ ኖሮኝ ሳለ?
ስድብ ከቶ አልክም ለዝምታው ዳኛ
ጤና ቢሰጠኝ ነው ሰርቼ ምተኛ
አላማርረውም ቤት ሳልገዛ ብዬ
የጎዳናውን ጉድ እያየሁኝ ባይኔ
ባለ መፅናናት ነው በፀጋው ማመስገን
ያለን ነው የሚበዛ ለእኛ ካልተሰጠን
ተመስገን ተመስገን
ይሄ ነው ክፍያው ደግሞ ለቀጣይ ቀን

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19