Get Mystery Box with random crypto!

ኳስ ሜዳ ድሮ ደጉን ጊዜ ማንቺስተር ከቼልሲ ዴስቲቪ ተገብቶ አርሰናል በ ሜሲ ..... | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ኳስ ሜዳ


ድሮ ደጉን ጊዜ
ማንቺስተር ከቼልሲ
ዴስቲቪ ተገብቶ
አርሰናል በ ሜሲ
........
ኳሱን ሲጠልዙ
በሜዳዉ ሲሮጡ
አንግሉን ሲመቱ
ከሜዳዉ ሲወጡ
......
አንዱን ከዜሮ
ጋር እያወዳደሩ
በቁማር በስሜት
ወተዉ ሲፎክሩ
.......
ጎድ ዛሬ ኮስ ሜዳ
ቀረና ሆነልህ ጦር ሜዳ
የቼልሲዉ የሜሴዉ
ጦር ሜዳ ተነዳ
.......
እየተጠለዘ
ደሙን እየዘራ
ምሽግ እንዳይፈልግ
ፔናሊቲ ፈራ
......
ነጭ ለተራገጠዉ
እራሱ የገጠበ
ስልጣን ሹመት
ላለዉ እየተጠበበ
......
አርሰናል ከሲቲ
ፕሪሜርሊግ ገባ
የቼልሲ ጨዋታ
ከሜዳዉ ሳይገባ
.....
ዳኛዉ ከሜዳዉ ዳር
ጺሙን እያሻሸ
በለዉ ተኩስ ብሎ
ጓዙን እያሸሸ
.....
ወንድሜ በል ንቃ
ሙያ በልብ ነዉ
ሀገርህ ተመታ
ቢልህ አትመነዉ
.....
ባንዲራ ሀገር ማለት
እሱወንድምህ ነዉ
ከሳቱ አትማግደዉ
ከደመህ አታርቀዉ
.....
በቦክሱ ሜዳእንኳን
ተማረኩኝ ብሎ
እንዴት ሰዉ ይገላል
መሀተሙን ጥሎ
.....
ሆ ብለህ ብቶጣ
ለብቻህ ብትሮጥ
ለ ሀገሬ ብትል
ህይወትህን ብትሰጥ
.....
ወይ አንተ የቼልሲ
የ ሊቨርፑል እንጂ
ማንም አይልህም
የ ኢትዮጵያ ረጂ

ኳስ ሜዳ

በፊፊ የተጻፈ
ቅኔ ራስ ግጥም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19