Get Mystery Box with random crypto!

#ተመስገን ፡ ፡ ፡ ገንዘብ እና ዝና ከኔ አንቺን ቀምቶኝ ፍቅራችን ሲሰበር የብር ኖት እና ያድናቆ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#ተመስገን



ገንዘብ እና ዝና ከኔ አንቺን ቀምቶኝ ፍቅራችን ሲሰበር
የብር ኖት እና ያድናቆት ጭብጨባን አንቅሮ እስከመትፋት ጠልቻቸው ነበር።
ገጣሚ ደራሲ ሰዓሊ ተዋናይ
መስለውኝ ነበሩ ልክ እናቴን ገዳይ።
ሀብታም ባለፀጋ ዲታ እና ከበርቴ
ፊቴ ባየው ቁጥር አሮ ደብኗል ቆሽቴ።


አሁን በቀደም ለት
የላቤን ክፍያ አወጣለው ብዬ ባንክ ተገኝቼ፣
ረብጣና ምንዳ ሆዱን ያሳበጠው አንዱን ባለግዜ እዚያው ተመልክቼ፣
አንቺን አስታውሼሽ በፊት ማያውቀኝን እኔም የማላውቀው፣
ጦስሽ ተቀስቅሶ ጥቂት ሰበብ ሽቼ አምሮኝ ነበር ላንቀው።


ደግሞም ሌላ ግዜ
አንድ ሁለት መድብል ለህዝብ ያደረሰ ዝነኛ ገጣሚ፣
እስካርፑን ጣል አርጎ ግጥሙን ሲያቀርብ ላዳራሽ ታዳሚ፣
እኔም ነበርኩና ከታዳሚው ተርታ፣
ያድናቆት ጭብጨባው ድንገት ሲበረታ፣
ዝናን ተከትሎ ልብሽ እንደከዳኝ ልቤን ቢታወሰው፣
መድብሉን ከጁ ላይ ወስደ ገነጣጥል የሚል ሀሳብ ደርሶ ሆዴን አላወሰው።


ከሰሞኑን ደግሞ
ከቤቴ እንደገባው ደክሞኝ ስራ ውዬ፣
አረፍ ለማለት ካልጋው ተንጋልዬ፣
በዚያው ለመቃኘት ትይንተ መስኮቴን ገና እንደከፈትኩት፣
አንዱ ባለዝና መድረክ ላይ ሲተውን መዘዝሽ ታውሶኝ አንድ ያለኝን ጥሪት በጡጫ ነደልኩት።


ይህ ብቻ አይደለም
ሙዚቃ አላደምጥም ስዕል ጠላው ላይኔ ከረፋኝ ድርሰቱ፣
አንቺን የቀማኝ ሰው የቅኔው ተቀኚ መስሎኝ ባለቤቱ።


እንዲያ ነበር በቃ መሀልቴ ሌሊቴ ካንቺ ጋር በድንገት እንደተለያየው፣
ካብታም ከዝነኛ በጎሪጥ በክፉ ሰርክ እየተያየው።
አልገባኝም ነበር ተሰውሮኝ ሀቁ ተዳፍኖኝ ምስጢሩ፣
ለካስ አይከበርም ነብይ በሀገሩ።
ተመስገን ነው ዛሬ ክብረት ይስጠው ገንዘብ ዕድሜ ይስጠው ዝና፣
ገልጦት ስላሳየኝ የተዳፈነውን ያን ያንቺን ስብህና።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockb
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19