Get Mystery Box with random crypto!

አዋልዷት አትሙት ገና በናት አብራክ ተጎናፈሽ ውበት ድክ ድክ ስትዪ ያኔ በልጅነት ተ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አዋልዷት አትሙት

ገና በናት አብራክ ተጎናፈሽ ውበት
ድክ ድክ ስትዪ ያኔ በልጅነት
ተንከባክባ ይዛሽ ክብርሽ ሳይነካ
በውበትሽ ተገርሞ ያየሽ ሳይረካ
.
.
.
ደርሰሽም ለእውቀት ሆነሽም ኮረዳ
ልጅነትሽ ያየ ሆንሽበት እንግዳ

ዳሌሽ ሲውረገረግ ከቀሚስሽ አልፎ
ያንን የልጅ ገላሽ ባንድ ሌት ተገፎ
ጡትሽም መሠለ የሚዋጋ ጦር
መላ አካልሽ አምሯል ከጫፍ እስከስር
የሚመኝሽ በዛ ላያገኝ ታክቶ
ልብላሽ አለ ሁሉም ጦሩንም አብልቶ
አይነ ግብ ገላሽ ለመሬት ሚያሣሣው
መነኩሴ ከገዳም ጸሎቱን የሚያስረሣው
ለአለ መንበርከክ ሽንጥሽን ገትረሽ
እጅ ላለመስጠት ደምሽን ተቃብተሽ
የተመኘሽ ወጋሽ..........
የጁ ሊያረግሽ..........


ሳትበገሪአቸው ጎልተሽ ስትታዪ
ሁሌ አሸንፍ! እንጂ እሸነፍ ሳትዪ
ትላንት የጎመጀሽ ገልብጦ እየወጋሽ
ልቡሽ ሳይበገር ድሉን እየነሳሽ
አልሸፈት አለ መቀነትሽ ጠብቆ
ፍራትና መራድ ፈርቶ ካንቺ ላይ ርቆ

ዛሬ ግን ደከመው ያንን ዣን ገላሽ
ታየ ህመምሽም ተስሎ ከ,ፊትሽ
የሚወጋሽ በዝቶ ፊትሽም ጠቆረ
ያንን ውብ ገላሽም ከወደዃላሽ ቀረ
.
.
.
የማን እንዶሆን እንጃ አርግዘሻል አሉ
የአብራክሽም ቁራሸሸ እንውሰደው አሉ

አላፈሩም ዛሬም ብት,ኚም አልተወሽ
አንግበው ተነሱ ሊያጠፉት አርማሽ
መድረሱ አይቀር ነው ደርሷል እርግዝናው
ቃልም ስጋ ሊሆን ደርሷል መወለጃው
ማማጥ ጀምራለች አይኗን ባአይኗ ልታይ
ልትይዝ ተሰጥኦዋ የተቸራች ከላይ

መውለድ አቅቷታል ሴቲቷ ተጎድታ
መተንፈስ ተሳናት ብርታቷንም አጥታ
ቸንቿንም አፍጥጧል አይኗ ተሠርጉዶ
"ያንን" ውብ ገላዋንም አለቀ ተቀዶ

ምጧ በረታባት ሀይሏ እያጠረ
አበባማው ፊቷ መጣ እየጠቆረ


ምን ይሆን ምትዎልደው?
.
.
እራብ ነዉ ምቶልደው ወይ ደግሞ ጥጋብ?
ልቶልድ ነው ይሆን እንደሷ የሆነ ውብ?

ምንድነው ምቶልደው?

እሳት ነው አበባ
ወይስ ደግሞ
ውሀ?
አጥፊ ነወ ወይ አልሚ
ወይስ
አለምላሚ?

ምን ይሆን ምቶልደው?

እንባዋን ሚያብስ የወጋት ሚወጋ?
የሚንከባከባት እንድትወርድ ከአልጋ ?
(ወይስ)
የተመታ ይሆን በፍቅርሽ ያበደ?
በመውደዷ እሳት ቀልጦ የነደደ?
(ወይስ?)
እራብ የሚያመጣ ነው ወይስ እረድኤት?
የሚፋጭስ ይሆን ከባሩድ ከጥይት?

ትውለደው አግዟት ለሷ ተሰፋዋ ነው
በኩራት ያኖራት ልቧ ያደነደነው
የምቶልደው ለሷ ጸጋ ነው ረድኤቷ
ያኖረችው በውነት ከስክሳ አጥንቷ
ልጇንም እንድስም ደሟ የፈሰሰለት
አትሙት አደራ እምዬን አዋልዷት

በቶኒ ይፋቱ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19