Get Mystery Box with random crypto!

ከግጥሞቼ ትህትና ትዕቢት ========== ከተፃፈልን በላይ ላንኖር ነገር አጉል መጨነቅ አጉል ማ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከግጥሞቼ
ትህትና ትዕቢት
==========

ከተፃፈልን በላይ ላንኖር ነገር
አጉል መጨነቅ አጉል ማማረር
ከማንደርሰዉ ጋ ሙግት መያያዝ
እንዴት በማለት ሙከራ እ/ርን ለማዘዝ
እየተጣደፍን ገደል እንዳንገባ
አሜን ነዉ መፍትሔዉ ሳይዙ ሰጣ ገባ
የሚሆነዉን በየዋህነት እየለመኑ
ከሀሳብ በፀሎት እንባ እየበነኑ
ከከንቱ መሻት ከአጉል ብክነት አድነን ብሎ
ልመና ይሻላል ያልክልኝ ይሁን ማለት በቶሎ
እንደቅርብ ወዳጅ ቀርቦ ማዋየት
እንደ አባት አይቶ በፍቅር አንደበት
ለመጠየቅማ ማንስ ከለከለ እንዴታ
ግና በዚች ትንሿ ልብ ትዕቢት ዘሯን ዘርታ
የኋሊት ከመሆን የጭራቆች ምሳ
ትህትናን ይዘን እንኑር እንዳንበሳ

ትዕቢት

ትህትና


በገጣሚ ሰላም ቢሻዉ
ለማንኛዉም አስታየትና ግጥም ለመላክ
@selamnen

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19