Get Mystery Box with random crypto!

ምነው በዛው ቀረሽ እመጣለሁ ብለሽ ቆሜ ስጠብቅሽ እዚ ነኝ ሳትዪኝ ምነው በዛው ቀረሽ እንገናኝ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ምነው በዛው ቀረሽ


እመጣለሁ ብለሽ ቆሜ ስጠብቅሽ
እዚ ነኝ ሳትዪኝ ምነው በዛው ቀረሽ
እንገናኝ ስትይ ቃልሽን አመንኩኝ
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፈጥኜ ደረስኩኝ
ከተባባልንበት ከመንገድ ዳር ቆሜ
አላፊ አግዳሚውን ስቆጥር ከርሜ
አንቺን በመፈለግ አይኖቼን ታምሜ
አትቀርም በሚል በተስፋ ታክሜ
ፈልጌ ሳጣሽ ግን ልቤን በጣም ከፋው
ደግሜ ሴት ላላምን ለራሴ ቃል ገባው

ጠብቄሽ ስትቀሪ
የያዝኩት አበባ ቅጠሉ ረገፈ
ስትቀሪ ጊዜ ሰማይ አኮረፈ
አውቃለሁ አምናለሁ
ምክንያት ይኖርሻል
ቢሆንም ቢሆንም
ቃል ማጠፍ ይጎዳል
የአማኝ ልብ ይሰብራል

እንገናኝ ብዬ ዳግም አልጠይቅሽ
አንቺ ካልተመቸሽ እኔ አላስገድድሽ
ግን ግን ለምን ውዴ?
አምኜ ስጠብቅ ምነው በዛው ቀረሽ።
ተጻፈ (በአብዱየእሙዬ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19