Get Mystery Box with random crypto!

dating #1 ፀጥ ያለ ቦታ ነዉ እኔ ዝም ብያለሁ እሱ ግን ያወራል ከፀጉሬ አንስቶ ጥፍሬን ይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

dating #1

ፀጥ ያለ ቦታ ነዉ
እኔ ዝም ብያለሁ እሱ ግን ያወራል
ከፀጉሬ አንስቶ ጥፍሬን ይታዘባል
ፀጉርሽ በጣም ያምራል ፀጉርሽ ነዉ አይደለ ብሎ ይጠይቃል

ደሞ ይተወዉና
ሽፋሽፋትሽ እስቲ ብሎ ይነካካዋል
ሲገርም እያለ ደሞ ይተወዋል

ያወራ ያወራና
ጉንጮቼን ከንፈሬን ጥርሴን ያሞካሻል
ሲደንቅ እያለ ደሞም ይተወዋል

ዝም ብዬ አየዋለሁ
እሱ ግን ያወራል
ያወራል ያወራል
ያወራ ይለፍፋል

ወረደ....ወረደ.... ከጥፍሬ ደረሰ
እዉነተኛ ነዋ ጥፍሮችሽ ያምራሉ
ሰዉ ያማልላሉ
ያወራል ያወራል
ዝም ብሎ ይለፍፋል

ሊገዛኝ ነዉ መሰል ልቤ አሁን ፈርቷል።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19