Get Mystery Box with random crypto!

1 ቀን ቢመለስ..... ቀኑ ይናፍቀኛል እማይመለስ ነገር አንዴ ሆኖብኛል 1ቀን መመለስ ቢቻል ኑ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

1 ቀን ቢመለስ.....

ቀኑ ይናፍቀኛል
እማይመለስ ነገር አንዴ ሆኖብኛል
1ቀን መመለስ ቢቻል ኑሮ ያኔ
ያን ቀን መልስልኝ እለው ነበር እኔ
እኔና አንተ ሆነን የፎረፍንበትን
ከአስተማሪያችን ጋር የተሯሯጥንበትን
በ15 ዴቃዋ ሻይ የጠጣንበትን
ከጓድኞቻችን የጠፈንበትን
ደሞም እጄን ይዘህ
አንገቴ ስር ገብተህ
የወደፊት ሚስቴ አንቺ ነሽ እያልከኝ
ከጓድኞቼ ፊት ሳሩን ያሰርክልኝ
በቬሎ መጋባት አደለም ብርቃችን
እኛ ተጋብተናል በዩኒፎርማችን
በፊርማ የተጋባን እስኪመስለን ድረስ
ተማሪ አስተማሪ እስኪረገን ርዕስ
እንዋደድ ነበር
እንዲያ ነበር ፍቅር
ተማሪ ቢሆንም ምንም ባይኖረው ብር
ከታክሲው ቀንሶ ይጋብዙኝ ነበር
አትዘልቁም አትልፉ
አትደርሱም ከአፋፉ
ያሉኝን ሰምቼ ትቼህ የሄድኩበትን
ዛሬም ረግመዋለው አንተን የተውኩበትን

ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19