Get Mystery Box with random crypto!

እቅጩ ያጣው እንቁ አንጎራጉራለሁ ባልተገራ ድምጼ እንባ አፈሳለሁ በአመዳም ገጼ እቀኛለሁ ቅኔ ሰ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እቅጩ ያጣው እንቁ


አንጎራጉራለሁ ባልተገራ ድምጼ
እንባ አፈሳለሁ በአመዳም ገጼ
እቀኛለሁ ቅኔ ሰም ወርቁን ላልፈታው
ግጥም እገጥማለሁ መቋጫ የሌለው
አብሠለስላለሁ የማያልቅ ሀሣብ
መብላት እመኛለሁ ያልቀመስኩት ቀለብ

ሀሣብ........

ሀሣብ..........

ሀ..ሣ.....ብ.........

የማይቋጭ ሀሣብ ወሣኔ የሌለው
ማየው እርቀቱ መቼም የማልደርሠው
ለምን እጄ አጠረ?
ለምን ልቤ አዘነ?
ለምን መቋጫ አጣሁ?
ለምን ውጤት ያጣ ትርጉምስ አልባ ሆንሁ?
ሀሳቤ መቋጫ አጣ
ተንጣጥቶ አለቀ ከምጣድ ሳዮጣ
ና ቀን እባክህ ሀሣቤን ድል መንሻ
ሚቀብረኝ ሚጎዳኝ አርቄ ማሸሻ

በመስከረም መሰለህ አበባ ይዘህ ና
ቀባረህ ቅረበኝ ክፉውን ቋጭና

በቶኒ ይፋቱ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19