Get Mystery Box with random crypto!

' ማነኝ???' :::::::::::::::::::::::።።።።።።። ዛሬ ስሽቀረቀር አፈር አልይ ባይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

" ማነኝ???"
:::::::::::::::::::::::።።።።።።።
ዛሬ ስሽቀረቀር አፈር አልይ ባይ
ልራመድ የከጀልኩ ሳላፍር በሰማይ
"ግን እኔ ማን ነኝ? "
የተቸገረውን ድሪቶውን ንቄ
ከመፈጠሪያዬ ከአፈር ርቄ
ተሸክሜ ዛሬ ይህ ድሪቶ ስጋ
የት ነው ብዬ ማላቅ አልፋ"ና" ኦሜጋ
.
.
...
እኔ ሰው ግን ማነኝ?


የመፈጠሪያዬ አፈር አይንካኝ ያልሁ
መቆሚያ ማረፊያ የልቤ እውነት ያጣሁ

እብለጨለጫለሁ
.
.
.
እሽቀረቀራለሁ
.
.
.
ሁሌ እኳኳላለሁ


ግን እኔ ማን ነኝ?

ማልሞት ማልቀየር አፈር የማይበላኝ
አጥንቴ እስኪቀር ምስጦች ማይቦጭቁኝ

ጸጉሬም በአፈር ማይተራመሠው
ምውደው ገላዬ ጉንዳን ማይበጥሠው

እንደ ተረዳሁት እንዳወቅኩት ግን ሰወ

ቢያምር
ባያምር
ቢዋብ
ቢሽቀረቀር
ቢደላው
ቢከፋው

ዞሮ የትም ላይቀር ገላ ለአፈር ነው
።።።።።።

በቶኒ ይፍቱ