Get Mystery Box with random crypto!

አላስብም መቼስ እጣዬ አደል ማጣት፣ ቢሆንም ይከፋል እድለቢስ ስትል እድሌ የምላት። ብትገፋኝ ብትን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አላስብም መቼስ እጣዬ አደል ማጣት፣
ቢሆንም ይከፋል እድለቢስ ስትል እድሌ የምላት።
ብትገፋኝ ብትንጠኝ ካሳቧ ብወጣ፣
ሽሽት ይይዘኛል መልሼ እንዳልመጣ፣
ለፍቅሯ ብሰዋ እራሴን አርግፌ፣
መንገዴን ብስተው እግሯን ተደግፌ፣
ዛሬ ጎረበጠኝ ህመም እየሆነ፣
የጨበጥኩት ተስፋ ከእጄ እየበነነ፣
የወጣልኝ ፀሀይ በፅልመት ዳመነ፣
ስቃዬ እየበዛ በፍቅር ማለዳ፣
ከአይኖቼ ማድጋ እንባ እየተቀዳ፣
መንፈሷ ካልቀና ልባዋን ካላራሰው፣
ባ'ካሄዴ ልፅና በመንገድ ልካሰው፣
.
.
ምን አልባት ስቃዬ በደስታዋ እንዲሽር፣
በመራቅ አምኜ ተስፋዬን ልሸርሽር

ናታን ኤርሚያስ
@UniqueDy

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19