Get Mystery Box with random crypto!

        የሰዉ ልጅ   የሰዉ ልጅ እኑስ ነዉ መቼም ማይሞላለት አካለ ጎዶሎ          በም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

        የሰዉ ልጅ

  የሰዉ ልጅ እኑስ ነዉ
መቼም ማይሞላለት አካለ ጎዶሎ
         በምኞት በተስፋ
ነገን እያለመ እየለፋ ቢያድር እያለፈ ዉሎ
         ቢጨምር መጨመር
ቢጎድል ኣብሮ መጉደል
        ቢገዝፍ ኣብሮ ገዝፎ
ቢቀል ኣብሮ መቅለል
       ባህሪዉ የሆነ
ምቾት እና እንግልት ሁኔታን መላበስ
      በኩነት መመካት
ሲያገኝ መደሰት ስያጣ የማልቀስ
      የሰዉ ልጅ ስንኩፍ ነዉ
ዛሬን ለማያዉቀዉ ነገን እያለመ
      ተማሪዉ ነገን ሲል
እየደጋገመ ቀለም የቀለመ
      ነጋዴዉ ፈጣሪን
ለወረት ልመና ዘዉትር የሚያስጨንቅ
      ከሀብቱ ሊጨምር
ከበርቴዉ ከደሃዉ በጉልበት ሚነጥቅ
     ገበሬዉ ነገን ሲል
ባዶ መሬት ኣርሶ እህል የሚዘራ
      ለነገዉ ነፃነት
ወታደር በሜዳ ጉድጓድ የሚጋራ
       የሰዉ ልጅ እንዲህ ነዉ
አሁንን ለማያዉቅ ነገን የሚያወራ
      መሄዱን እረስቶ
ኋላ መጠለፉን ሁሉም በየተራ

_-_-_-_-_-_- -_-_-_-_-_-_
           #ገብረስላሴ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19