Get Mystery Box with random crypto!

የእኔን ፍቅር መግለፅ በቃላት ሲያቅተው በድርጊቱም ገልፆ ለሱ አልበቃ ሲለው እስካሁን የኖርኩት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የእኔን ፍቅር መግለፅ በቃላት ሲያቅተው
በድርጊቱም ገልፆ ለሱ አልበቃ ሲለው
እስካሁን የኖርኩት የቆየው ህይወቴ
ላንቺ ነው የምኖረው እስከ እለተ ሞቴ
እወድሻለሁኝ እያለኝ አባቴ
ፍቅር ሲዘራብኝ ባልታረሰዉ ልቤ
አፍታም አልፈጀበት ሲሳሳለት ቀልቤ
ህይወትን በፍቅር በንፁህ ልቦና
ለሚወዱት መሞት ሲልቅም አለና
ታምኖ መሰዋት ነዉ ለህይወቱ ቀና
እያለኝ አባቴ
ልዩ ጥበብና ልዩ ማስተዋልን ፈጣሪ ሲቸረው
ችሎታዉን ልቤ ሁሌ እንዲዘክረዉ
አለና እንዳስበዉ
ባዶ እጁን ተጓዘ ዉስጤን እያመሠዉ

ፅጌሬዳ አስናቀዉ