Get Mystery Box with random crypto!

አንቺ ባለሽበት ፣ሚባለውን እንጃ እኔ ባለሁበት ፣ ወሬ እንደጠብ መንጃ የታጠቀ ሞልቷል ፣ ቢደላም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንቺ ባለሽበት ፣ሚባለውን እንጃ
እኔ ባለሁበት ፣ ወሬ እንደጠብ መንጃ
የታጠቀ ሞልቷል ፣ ቢደላም ቢከፋም
ጆሮ አይሰማው የለም
የሚበላ እንጂ ፣ የሚባል አይጠፋም !
#ይባላል !
።።
ለምሳሌ ያህል
ትጥቃችን ባያልፍም
ከዱላ ከድንጋይ ፣ ግፋ ቢል ከክላሽ
ወዮለት ለጠላት ፣ ኋላ እንዳይበላሽ
ኒውክለር ሲመካ
አደቧን ትያዝ ግብፅ ፣ ትረፍ አሜሪካ
አላርፍም ካሉ ግን ፣ ወየው ለሁለቱም
ባለም ፊት ፈስ በፈስ
እንዳናደርጋቸው
በእጃችን ነው ያለው ፣ ደብተራም መተቱም
ይባላል
፣፣፣፣
ለምሳሌ ያህል
ሰማንያ ሺህ ዳቦ ፣ ሊያውም በአንድ ቀን
ሊጋገር ነው ሲሉን ፣
በምን መብራት ብለን ፣ አናውቅም ጠይቀን
እንዲሁ በማመን ፣ ሆዳችን ይሞላል
በመሪ አንደበት
ደም ያፀናው ሰንደቅ ፣ ጨርቅ ነው ይባላል።
።።።
እኔ ባለሁበት ፣ በመኖሬያዬ ሀገር
ከፀሐይዋ በታች ፣ የማይባል ነገር
አንዳች አይገኝም ፣ ሁሉ አፉን ያክላል
የሚለው ያጣ ሰው
የተባለን ነገር ፣ "አይባልም "ይላል
።።
የሆነው ሆነና ፣ ባለሁበት ሀገር
የማይባል ነገር
አጋጥሞኝ አያውቅም
ለምሳሌ ያህል
አባይ በአምስ አመት
ተገድቦ ያልቃል
በኢትዮጵያ ምድር ፣ ፀሀይ አትጠልቅም
አስራ አንድ ፐርሰንት
ሀገሪቱ አድጋለች ፣ በኑሮ ብንደቅም
ስልጣን የህዝብ ነው ፣ ግን ለህዝቡ አንለቅም
ይባላል

ለምሳሌ ያህል
ባይቆጥራቸው እንጂ፣ ዘንግቶ ምናልባት
ጠቢቡ ሶሎሞን
ከጠቢቡ በላይ ፣ አይበልጥም በእቁባት
#ይባላል
በላይ በቀለ ወያ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19