Get Mystery Box with random crypto!

። ፍጡር ከስይጡኑ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። አስፍተን ሄደናል እንዳወቀ ተምረን አትብሉት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

። ፍጡር ከስይጡኑ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አስፍተን ሄደናል እንዳወቀ ተምረን
አትብሉት ያሉንን በለስንም በልተን

የረድኤት ማነስ ፍቅር የማጣቱ
ትውልድ መበጣጠስ የእምነት ውድቀቱ
ቀኙ ጎዳናችን በግራ ረግጠን ሄደን
መዋደድ ረዴት የውነት ፍቅር አጣን

ተባእት ከተባእት መስርቶ ትዳሩ
እንስት ወንድ ተወ ከንስት ሆነ አዳሩ

ማን ልበል ባልዬ ማንስ ልበል ሚስት?
ቀንድ አውጥቶ እያየሁ ተባእት ከንስት

ጉድጓድ ቆፍረናል የራሳችን መግቢያ
እውነታውን አጥብበን አስፍተን መለያ

ስይጡኖች ይብቁን አንሻቸው እኛ
ፈቀቅ ብለን እንቁም ከጋኔን መገኛ
እኛን ከሚያስመታን የስይጡን መጋኛ
ከሀሰት እርቀን እኑን የውነት ዳኛ

እኛን ከሚያስረን እንዳናልፍ ከደጅ
በላንጣ ከሚያረግ ከቀና ወዳጅ

አውቀነው እንራቅ ይህ ክፉ ጎዳና
ከልባችን ይስረጽ የኖረ እውቅና
ወገናችን ይትረፍ ከስይጣኔ ጫና
ስልጣኔ ይሁን ጥለን ይህ ገበና

ያለም ስልጣኔ ትሁን በኛ ዘንድ
ቆመን በክብር ቃል ጸንተን አምረን ባንድ
ርቀን ከዘንዶው ከክፉው ወጥመድ
ከእሳቱ እንራቅ አውቀን ከመንደድ

(መርሀችን እናርግ)

"ስይጣኔን ጥሎ ስልጣኔን ባንድ"



በቶኒ ይፋቱ