Get Mystery Box with random crypto!

እናቴ ጀግናዬ ነሽ መከታ አለኝታዬም ነሽ ክብርሽን የጠበቅሽ እራስሽን ያላስደፈርሽ የሴቶ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እናቴ
ጀግናዬ ነሽ
መከታ አለኝታዬም ነሽ
ክብርሽን የጠበቅሽ
እራስሽን ያላስደፈርሽ
የሴቶች ተምሳሌት
ምሳሌ የአንድነት
የፍቅር አብነት
የሠላም ማብሰሪያ
የፍቅር መጀመሪያ
የደግነት ጥግ አንቺ ነሽ
ደከመኝ ሰለቸኝ
ተራብኩ ተጠማሁኝ
ጫማ ልብስ አጣሁኝ
ሳቲዪ ተሸነፍኩኝ
እያልሽ አሸነፍኩኝ
አልፋለው እሄም ቀን ያልፋል
መከራ ችግርም ይሄዳል
ድህነትም ይሰደዳል
ፍቅርም ይመጣል
ሰላምም ይሰፍናል
ብለሽ እዚህ ደረስሽ
ሁሉንም ችግር አልፈሽ
መከራንም ተሻግረሽ
ችግርን አሸንፈሽ
ድህነትን ተቋቁመሽ
ጥላቻን አስወግደሽ
በፍቅር ከሁሉም በልጠሽ
በትዳርሽ የተሳካልሽ
በብልሃት በዘዴ ከሁሉም በላጭ ነሽ
የኔ እናት ፍቅር ነሽ
ስምሽ ይጣፍጣል ሲሉት ወላንሳ
ግርማ ሞገስ አለው እንደ አንበሳ
አልፈሽ ያን ሁሉ አበሳ
እዚ ላይ መድረስሽ ይገርመኛል ወላንሳ
በደግነትሽ ያልተገኘልሽ አቻ
ለችግር ሁሉ ያለሽ መፍቻ
ለተዘጋ በር የማታጪ መክፈቻ
እንዳንቺ ላሉ ሴቶች የምትሰጪ ማበረታቻ
እናቴ መሠረቴ
እምዬ ሀብቴ
ላኑርሽ ከቤቴ
ነሽና በረከቴ
ልጡርሽ ዘላለም
እንዳንቺ ለኔ የሆነ የለም
ኑሪልኝ ለዘላለም
እድሜ ይስጥሽ ጤና
ለዘላለም በቤቴ ላኑርሽ ይሳካልኝና
ውለታሽ ብዙ ነው
የማያልቅ ብከፍለው
አነጋገርሽ የሆነ ረቂቅ
ቅኔሽ ልብ የሚሰርቅ
ፈገግታ ሳቅሽ የሚናፈቅ
የሰጠሽኝ ፍቅር የማይሰረቅ
ምን ልበልሽ ቃል አጠው
ምን ላርግልሽ አቅም አገኘው
ውለታሽን በምን ልክፈለው መክፈያ አጣው
የማታ ማታ
አረፍ ስል ከመኝታ
ሁሌም በሄድኩበት ቦታ
ትመጫለሽ በትዝታ
ብትለዪኝ ላፍታ
ይጠፋል ከኔ ደስታ
ሌላ ምን እላለው እንዲ ልበል እንጂ
እናቴ ይስጥሽ ጤና
እድሜም ይጨምርና
ፍቅር አይንፈግሽ
ሰላምም ይስጥሽ
ለዘላለም ኑሪልኝ ስለምወድሽ
እፈልጋለው እናትነትሽን
እናፍቃለሁ ደግነትሽን
እናቴ እምዬ ለዘላለም ኑሪልኝ
እወድሻለሁ ሁሌ ካጠገቤ ሁኚልኝ
አምላክ እድሜ ይስጥሽ ቆዪልኝ
ገጣሚ
ሜሮን ሲሳይ