Get Mystery Box with random crypto!

እኛ የአባቶቻችን ልጆች አይደለንም (ታደሰ ደምሴ) ከሳት ተወልደናልና ረመጥ መሆን ካልታደልን ' | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እኛ የአባቶቻችን ልጆች አይደለንም
(ታደሰ ደምሴ)

ከሳት ተወልደናልና ረመጥ መሆን ካልታደልን
"መፋጀት" ግብራችን ተሽሮ ሌላ እሳት ነኝ ባይ ከፈጀን

አዕላፍ ያለስስት ተዋድቆ ሳትጎድፍ የተረከብናትን ሀገር
የቸልታ አዚም ከረታን ክብሯ በባለጌ ሲደፈር

ከዕርስታችን አልፎ የመጣን
በትር አንስተን ካልቀጣን
የወገን ትዳር ሲፈታ በእንቅልፍ አክናፍ ውስጥ ከነጎድን
መቼ የአባቶቻችን ልጆች ሆን!?

አሙቆ እንዳላሳደገን በወኔ የመቻል እቅፍ
ታሪካችንን ለመድገም ካሰረን የፍራት ሰንኮፍ

ትናንት ቀን ያጀገነው ኮብልሎ ያ የፈሪ ልጅ
ድንበራችንን ተላልፎ ሞፈር ሲቆርጥ ከኛ ደጅ

ክንዳችን በራድ ከሆነ ውሎ አድሮ ጠላት ሲያገረሽ
ምናልባት "ዲቃላ" እንዳንሆን እስኪ ዕራሳችንን እንፈትሽ!!!

#ሼርርርር

for any comment

@Maryam21161