Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ ስትከዳኝ አይቻታለሁ እንደገፋችኝ ትገፋ እያልኩ እረግማታለሁ። ~ ዘወትር ሙሾ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ።
~
ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የዕንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።

የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።

የምድር የቀላይ ጥፋት
በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው
ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ ።

ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።

የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅ
በዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ።

ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ
ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ።

በአበባው መላኩ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19