Get Mystery Box with random crypto!

ኤሎሄ (ታደሰ ደምሴ) 'ሺ' ሰው ባንድ ጀምበር በጦር በገጀራ ሲረሸን እያየን ምነው ኢትዮጲያዊ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ኤሎሄ
(ታደሰ ደምሴ)

"ሺ" ሰው ባንድ ጀምበር በጦር በገጀራ ሲረሸን እያየን
ምነው ኢትዮጲያዊ ከእግዜር 'ምታስታርቅ አንድ ራሔል ያጣን!?

እንዲህ ባደባባይ በመንጋ ተመክሮ በሴራ ስንጠፋ
የግፍ ባህር ከፍሎ ከፈርኦን የሚያስጥል ምነው ሙሴ ጠፋ!

ያ የጎልያድ ልጅ ቀን ደገፈኝ ብሎ እንዲህ ሲዝትብን
እንዲያው ለምን ይሆን ወንጭፍ የሚያነሳ ዳዊት የቸገረን!!!

እባክህ እግዜሩ...
ከእያሪኮ ልቆ ከናታችን ገላ በቀል ተገንብቷል
እያሱን ላክልን የሰላሟን ምድር "ከንዓን"ን ናፍቀናል!

እባክህ እግዜሩ...
አቅፈን ባሳደግነው በዛ ባለጌ ጥርስ እጃችን ተነክሷል
ሀይል በፀጉሩ ቋጥሮ እባብ 'ሚገድልልን ሳምሶን ግድ ይላል!!!

እባክህ እግዜሩ...
እባክህ...እባክህ...
ከምድርህ ተነቅለን ትርክት ሳንሆን
ከለመንህ ሁሉ አንድኳ ላክልን
ጓዳችንን ታውቅ የል...!
'ሚደገፈን እንጂ የምንደገፈው መንግስት እንደሌለን!!!

#ሼርርርር

@Maryam21161

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19