Get Mystery Box with random crypto!

''አትርሺው'' ።።።።።።።።።።።።።።።። አይረሳም ለኔ ያንን ሁሉ ጊዜ አረሳው ብሎኛል የውስጤን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

""አትርሺው""
።።።።።።።።።።።።።።።።
አይረሳም ለኔ ያንን ሁሉ ጊዜ
አረሳው ብሎኛል የውስጤን አባዜ
እንዴት ይረሳሻል ጭቃ ያቦከንበት
በማያቅ ልባችን ፍቅርን ያየንበት
እረሺኝ ለኔ ባዮን እሱን ከምትረሺ
ያን ሁሉ ህግጋት ባንዴ ከምጥሺ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"አትርሺው"
አትርሺው እባክሽ እኔ ብትረሺኝም
ያሳለፋነው ጊዜ አስታውሺው ሁሌንም
እኔ አ..ረሣውም ከልቤ አዮጣም
ያንን ጣፋጭ ጊዜ ሚረሳ የላኝ ልብም

"ይረሳል ወይ?"

እስኪነጋ ጨንቆን አንድ ላይ እስክኖን
ጸሀይ ስትገባም በናፍቆት ተላቅሰን
እንዴት ይረሳሻል ያን ሁሉ ትዝታ
እኔስ ልብ ተቀብሯል መቼም ላይገታ
...........
ካሳለፍነው ይልቅ ተለያይተን ብንኖር
ምትጠብቂኝ መስሎኝ ቃላችን በክብር
ግን ዛሬ እረሳሽ ሁሉንም ቀበርሺው
ቃል የገባሽውም ብለሽ ላረሳው

"አትርሺው"
እርሺው ቢሉሽ እንኳን እኔን ላይሆንሽ
ጉጉታቸው አርገው ለነሱ ሊያረጉሽ
አታውጪው ከልብሽ ዘላለም አኑሪው
ልብሽ ባዮደውም በብእር ቅረጪው
አትርሺው
እኔ ብትረሺኝም ትዝታው አትርሺው



በቶኒ ይፋቱ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19