Get Mystery Box with random crypto!

ቀን አላት ሀገሬ (ታደሰ ደምሴ) (@Maryam21161) ይመለሳል ሳቋ ይነጥፋል እምባዋ እንዲህ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቀን አላት ሀገሬ
(ታደሰ ደምሴ)
(@Maryam21161)

ይመለሳል ሳቋ ይነጥፋል እምባዋ
እንዲህ ጠልቃ አትቀርም ትሠርቃለች ፀይዋ

ካብራኳ ክፋዮች ገለል ይላል መርዶ
ከላይ የታዘዘ አዲስ ሰላም ነጉዶ!

ቀን አላት ሀገሬ...
አንገቷን ቀልምማ አቀርቅራ አትቀርም
በክብር ተገልጣ ትነግሳለች ዳግም!!!

አዕላፍ ዲቃላዎች ክደው ቢነክሷትም
ታምኗት የመነነ ልጅ አልቸገራትም!

ቀን አላት ሀገሬ...
ከፍ! ይላል አርማዋ ይወጣል ሰገነት
በእቶን ይጋያሉ ዛሬ የነከሷት!

ቀን አላት ሀገሬ...
በሰማይዋ አክናፍ ላይ እርግብ ያንዣብባል
ፍቅር ተራው ሲደርስ ዘንባባ ይጥላል

ሆነን አንቀርም ቁርሾ ማንኮላቻ
ይ'ን ቀን እናያለን እድሜ ይስጠን ብቻ!!!

#ሼርርርር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19