Get Mystery Box with random crypto!

አንቺ እስስት እረፊ እረፊ ብዬሻለው ተይ እረፊ አንቺ እስስት ተይ እንዳልልሽ በጥፊ በኋላ ረግ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንቺ እስስት እረፊ
እረፊ ብዬሻለው ተይ እረፊ
አንቺ እስስት ተይ እንዳልልሽ በጥፊ
በኋላ ረግጬሽ እንዳትከፊ
ተይ አንቺ እስስት
እረፊ አንቺ የራስ ምታት
እኔም ወገን አለኝ
እኔም ደጋፊ አለኝ
ከእስስቶች መሀል ያልሆነ
ከካሃዲዎች ጋር ያልተቧደነ
ካንቺ ጋር ያልወገነ
አለኝ ወገን አለኝ አጋዥ
ተይ አትሁኝብን አደንዛዥ
አትቀያየሪ በሄድሽበት
አትስሪ ተንኮል በቆምሽበት
እንደ እርጎ ዝንብ በሁሉም ቦታ አትበይ ግብት
አትፈልጊ ሁሉንም ለማዘዝ
አንዳትመኚ እኛን ለማደንዘዝ
ከብዙሃን መሃል ከጥቂቶች መንደር
የመጣሽው ለመበታተን የኛን ሰፈር
መዳኒት ከሆነው ልትቆሚ ከኛ አፈር
የመጣሽው ከዛ ከመጥፎ ሀገር
አታቆሽሺ የኛን ሀገር
ከዛ ከሆነ ረመጥ
ከበዛው ድጥ
ከተሞላበት እስስት
ከተትረፈረፈበት ወንፊት
የመጣሽው አንቺ እስስት እረፊ
ከዛ ከመጥፎ ቦታ ያለሺው ተይ እንዳትገረፊ
የኋላ የኋላ ግን እንዳትዋረጂ
ስትቆይ ስትቆይ ግን እንዳታብጂ
አላርፍ ብለሻል እንዳትጎጂ
ብያት ነበር እኔ
መክሬያታለው እኔ አስቤያት እንደወገኔ
አልጨከንኩባትም ቢሆን እንደምኞቴ
አስተናግጄያት ነበር አስገብቼ ከቤቴ
ስናወጋም በወሬ መሃል
ነግሬያት ነበር ስለ አባቴ ጀግንነት
ስለ እናቴ ደግነት
ስለ እሷ ጀግንነት
ስለ አያቶቼ ነፃ አውጪነት
ስለሁሉም ነገር
አስጠንቅቄ ነግሬ ነበር በዝርዝር
ታዲያ ምን ያደርጋል አልሰማ አለች እሷ
ግን ከንቱ ድካም ነው
እስስት አይቀየርም ያው እስስት ነው
እምቢ ካለች እንግዲያው
ትምጣ አሳያታለው
እስስቶችን እንደማልፈራ
ለነብሳቸው እንደማልራራ
አሳያታለው ትምጣና
ድሮም እሷን መምከሬ እኔ ነኝ ጥፋተኛ
እስስት ያው እስስት ነው
አይቀየርም አሁን አውቄአለው
እንዳልነበረች አድርጌ እኔው እጨርሳታለው
ገጣሚ
ሜሮን ሲሳይ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19