Get Mystery Box with random crypto!

ኑ በተስፋ እንኑር! (ታደሰ ደምሴ) እንዲያ ...በደቦ እየጠጣን ከጠላቤት አለም በሀሳዊ ትምቢት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ኑ በተስፋ እንኑር!
(ታደሰ ደምሴ)

እንዲያ ...በደቦ እየጠጣን ከጠላቤት አለም
በሀሳዊ ትምቢት ሰክረን ያለምነው ህልም

እንዲያ በደመነፍስ...
ከስጋ አምሮት እቶን ወድቀን እየጋየን
ያልኖርነውን ህይወት...
በረከሰ ምላስ ፅድቅ እየወለዠን
የቆጠርነው ሱባይ ተሳልቆ ከከዳን

ኑ! በተስፋ እንደር...
ኑ! በተስፋ እንኑር...

እንበል "መኸር ደርሷል ቀን ይወጣል" ዳግም
ምን ሳይሰምር ቢቀር ተስፋ አይነፈግም!!!

#ሼርርርር

@Maryam21161

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19