Get Mystery Box with random crypto!

የሴት ልጅ ነኝ እኔ ሴት ነኝ ጀግናዋ እኔ ሴቷ ቆራጥ ብርቱዋ በሴትነቴ የምኮራዋ በሀገር በስራ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የሴት ልጅ ነኝ

እኔ ሴት ነኝ ጀግናዋ
እኔ ሴቷ ቆራጥ ብርቱዋ
በሴትነቴ የምኮራዋ
በሀገር በስራዬ ቀልድ የማላውቀው
ብልጭልጭ ነገሮች የማያታልሉኝ
በስራ ቢሉኝ በትምህርት
በጉብዝና ቢሉኝ በጀግንነት
በሰላም ቢሉኝ በጦርነት
በዘዴ ቢሉኝ በብልሃት
ሾፌር ቢሉኝ አብራሪ
ተማሪ ቢሉኝ አስተማሪ
ዳኛ ቢሉኝ መርማሪ
ተቀጣሪ ቢሉኝ አስተዳዳሪ
ፖሊስ ቢሉኝ አካሚ
በሁሉም ከሰው የማላንስ
ጀግናና ፈጣን ልክ እንደ ነፋስ
ከወንድ የተገኘው
ከሴት የተወለድኩ
ከሴት የተፀነስኩ
የሴት ልጅ እንደሆንኩ
ወንድም ሴትም ሆኜ
ከወንድ ተፈጥሬ ከሴት ተወልጄ
አለው እስከዛሬ እየተባልኩ ልጄ
የሴት ልጅ ነኝና በሴትነቴ አላፍርም
የሴት ልጅ መባል ስድብ አይሆንም
ፀንሳ ዘጠኝ ወር በሆዷ ይዛኝ
ተቸግራ አምጣ ወልዳኝ
አራት እመት አጥብታኝ
አስተምራ ለወግ ለማዕረግ ላበቃችኝ
ላሳደገችኝ ለተንከባከበችኝ
ታዲያ ለምን ትሰደብብኝ
ታዲያ ለምን ትጠላብኝ
የሴት ልጅ መባል ስድብ ስለመሰላቸው
ስድብ ለሚያደርጉት አእምሮ ለሌላቸው
ማሰብ ማሰላሰል ስላቃታቸው
የማን ልጅ ልባል
ካልተባልኩኝ የሴት ልጅ
የጦር አውራ ሆና ጦሩን የመራች
ሴት ሆና እንደወንድ የሠራች
ከወንዶች እኩል የዘመተች
የጀግኖቹ ጀግና የሆነች
እኔ የእቴጌ ጣይቱ ልጅ ነኝ
የእቴጌ የኢትዮጵያዊቷ ልጅ ነኝ
ቆራጥና ጀግና በሀገር የማትደራደር
ሀገርና ርስቷን አሳልፋ የማትሰጥ የሆነች ቸር
አንድ እምዬ እሷ ነች እቴጌ ጣይቱ
እኔ የሷ ልጅ መሆኔ
ያስመሰክራል ጀግንነቴን
ለስራ ለትምህርት የምሰጥ ቅድሚያ
ሳይሰሩ መብላትን የምፀየፍ ቅሚያ
ጠላቴ የሆነዉ ሌብነትና ዝርፊያ
ተምሬ ጠንክሬ እዋጋ ሙስናን
ሰርቼ ለሀገሬ አጠፋለው ጉቦን
በርትቼ በሃገሬ አጠፋለው ድህነትን
እሰራለሁ ታሪክ ሆኜ ሴት
እሠራለሁ ለሷ ላሳደገችኝ እናት
ለእምዬ እንደሆንኩኝ የሴት ልጅ
ሴት ነኝ የሴት ልጅ

[ ሜሮን ሲሳይ ]


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19