Get Mystery Box with random crypto!

*እስክትድኝ ልበድ** አበርችኝ የኔ አለም አጽኒኝ የኔ አለኝታ በገተሩሽ ሸንጎ ስለ ሀቅሽ ልርታ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

*እስክትድኝ ልበድ**

አበርችኝ የኔ አለም አጽኒኝ የኔ አለኝታ
በገተሩሽ ሸንጎ ስለ ሀቅሽ ልርታ
ልጩህ በተራራ በሜዳበአደባባይ
ጉድሽን ልተርክ ይመስክረኝ ሰማይ።
እሷ ሰው በላ ናት እያልኩኝ ልናገር
ሲቃ ምርኩዟ ነው እያልኩኝ ልናገር
አበደች ይበሉኝ ከጠበል ልነከር።
ቄሱ ይድገሙልኝ የእብደቱን ማርከሻ
ጠንቋይ ይንተባተብ ድግምቱን ማደሻ
እንዳልሆነ ይሁን በርትተሽ አበርቺኝ
ጤንነት ምኔ ነው? አንቺ ታመሽብኝ!!
ይልቁንስ ልጩህ ሰው አርጊኝ እናቴ
ድክመትና ጉልበት ህመም መድሐኒቴ
ልንገራቸው ዛሬም የአርቡን ለታ ሸንጎ
ጌታ መሰቀሉን የእሾህ አክሊል አርጎ
የመሳሙን ቀመር የይሁዳን ደባ
የመስቀሉን ስቃይ የወላዷን እንባ
አበርቺኝ ልናገር ጩኸቴ ያድክመኝ
ቀዬው ይንሾካሾክ አበደች ይበለኝ
ወትሮስ እየነኩሽ ምን ጤንነት አለኝ??
ወለምታ ማያጣሽ አንቺ ልማደኛ
የልጆሽ ደም ነው የመምሽ መዳኛ።
ከጽዋሽ አጠጪኝ ባንቺነትሽ ልስከር
በጠጅሽ ሰምጬ በጠላሽ ልንዘርዘር
ያናግረኝ ሞቅታ እንዲህ ነው ትርጉሙ
ስካርና እብደት ነው የነጻነት ስሙ!
ደግሞ ልበድልሽ ካድባር ልንተፋተፍ
ጌታን ተደገፊ እኔ አንቺን ልደገፍ።
ፍጥረቱ ይዛባ ቀየሽ ይተራመስ
ቅኔ ትስገድልሽ ይጀብሽ መወድስ
ደግሞ ላቀማጥልሽ በንኩ ብዕሬ
ደግሞ ልገዝትሽ በጠና ስካሬ
በታሰረ ምላስ በወልጋዳ አካሄድ
በቡትቶ ጨርቄ እስክትድኝ ልበድ
ጤነኛ አልሆነሽም እብድ ነው ያንቺ ገድ!
ደግሞ ልቀዣብር ደግሞ ልቀባጥር
እንባሽ ነው መጠጤ በጠራራ ልስከር
እንባሽ ነው ጥንስሱ አረቄ የሆነኝ
ጨጓራዬን ልጦ ራሴን ሚፈልጠኝ
እንባሽ ነው እንባዬ እንባሽ ነው ህመሜ
ከአንድ እንስራ ገብቷል ደምሽና ደሜ።
ተውኝ ልበድበት
ተውኝ ልስከርበት ጤናን አልመኝም
ስንትዜ ነው ህይወት ስንትዜ ነው አለም?
ሀገሬ እየደማች እኔ እንዴት ልታከም?
ተውኝ ልበድላት መድሀኒት አልሻ
ስካር ሚያፋታኝ እብደቴን ማርከሻ።
አብጄም ሰክሬም እሷን ብቻ ልስበክ
ነፍስና ስጋዬ ለስሟ ይብረክረክ።
እኔ መታመሜ እሷን ከፈወሳት
አንድ ጊዜ ቀርቶ እልፍ ልበድላት!
ያኔ ነው የምድን ያኔ ነው ሚሻለኝ
ህመሟን ወርሼ ጤና ስትሆንልኝ
ያኔ ነው ሚገራ ይህ ከርዳዳ ድምጼ
ሀገሬ ስትድን ነው የሚወርደው ለምጼ!!
እሷው በሽታዬ እሷው ናት የኔ ሐኪም
እሷው ናት ድክመቴ እሷው ናት የኔ አቅም
እብደት ጤንነትን፣ህይወትና ሞትን ከርሷ ውጭ አላቅም!!!



ኢትዬጲያዊነት
01/13/13
ሳሮናዊት እንድሪስ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19