Get Mystery Box with random crypto!

የጎዳናዋ እናት ወላጅ ቤት ባይኖረኝ፣ የሥሜ መጠረያ እናት ግን አለችኝ፣ ዋርካ መጠለያ ጎጅዋ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የጎዳናዋ እናት


ወላጅ ቤት ባይኖረኝ፣ የሥሜ መጠረያ
እናት ግን አለችኝ፣ ዋርካ መጠለያ

ጎጅዋ የማትነፍግ፣ሠለቸኝ የማታቅ
ኪስ ጉስቆላን አይታ፣ተጸይፋ የማትንቅ
ፊቷ የማታጠቁር፣በክፉ የማታይ
ካላት የማትሠሥት፣የተቸራት ከለይ

አባት፣ዘመድስ፣ቤት ኧረ እኔ ለምኔ
እናቴ አለች ብዬ፣ይበቃል ማመኔ

ምድሯ መኝታዬ፣ዳገት ቁልቁለቱ
ለዛልኩኝም እለት፣ያደርገኛል ብርቱ

ሠንደቆ ካባ ነው፣በውርጭ አያስመታ
አመኖም ለተካበው፣ለልብ አያስረታ

አይርበኝ ምግብ ነው፣ስሟ ላንደበቴ
ይብቃኝ ለሧ ልኑር፣ምለው የለኝ ቤቴ

እጄ ስዘረጋ፣ባንድ አፍት ምትሞላ
ጸሀይ ስትበረታ፣ምቶነኝ ከለላ

ታዳ ቤት ለምኔ፣ድሎት ነው፣ይህ ኑሮ
ይበቃኛል ይቅር፣ቤቴ ኧረ አልበል ጓሮ

አይሠለችም ስሟ፣ላንደበ ኩራት ነዉ
በፍቅር ለጠራው፣ኢትዮጵያ የሚለው

ኢትዮጵያ ኩራት ናት
ኢትዮጵያ ምግብ ናት
ኢትዮጵያ አርኪ ናት
ኢትዮጵያ እራብ ናት
" "ጥማት ናት
ኢትዮጵያ(+2)እናት ናት
ኢትዮጵያ ፍቅር ናት
ኢትዮጵያ(+2)ሀገርም ናት
ኢትዮጵያ ቤትም ናት

ለተከፋ አንደበት፣መጽናኛ ሙዚቃ
ቢሰሙት ቢዘፍኑት፣ማይሠለች ማይበቃ
ጥንካሬዬ ናት፣የመንፈሴ ምግብ
በመንገዷ ብኖር፣የማይነካኝ እራብ

ወላጅ የለኝ ብዬ፣ከቶም አልከፋ
ዘላለም ምትበራ፣ሻማ ናት፣ማትጠፋ
አባት፣እናት፣ወንድም፣እህቴም እሧ ናት
አትንኳት ትለምልም፣የጎዳናዋ እናት

በቶኒ ይፋቱ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19