🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ዛቅ እፍስ  ከሰማይ ከከዋክብት መሃል መዳፎቼን  ዝርግት እንደው 'ላመል ታህል አንዲቷን  ለአፍ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ዛቅ እፍስ  ከሰማይ ከከዋክብት መሃል
መዳፎቼን  ዝርግት እንደው 'ላመል ታህል

አንዲቷን  ለአፍሽ
ጥለት  ከመሰለው  ስስ  መስመሮች  መሃል
ብርሃን  ፈንጥቆ  ደምቄ  እንድስምሽ

መንታ  ለአይኖችሽ
ጸሊም  ፊቴ  ፈክቶ
አብርቼ  እንድታይሽ

አንዲቷን  'ላፍንጫሽ ለተንሰለከከው
'ብስብስ መዓዛዬን አርቅቆ ቢልከው

ቆንጥሬ ብሰጥሽ
ጥቂቱን   ለጭንሽ
የ'ርግማን  ምጥሽን
በዘመን  ያረጀ ወልድን  ሳትማልጂ 
ጣርሽ ቢሻርልሽ

አልቦ ተስፋው እኔ በቅዠት እጆቼ

ዛቅ እፍስ  ከሰማይ ከከዋክብት መሃል
መዳፎቼን  ዝርግት እንደው 'ላመል ታሀል።
አድርጌ  ልቸርሽ
ከልቤ  ባሻገር
ሙላተ  ዓለሙን  ላንቺ  እንደምለግስ
ትዝ  ትውስ ቢልሽ።

ብሩክ (ዝብርቅርቅ)

።።።።።።።።። ።።።።።።።
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19